Metasebia Dereje Abate

የአፍሪካ ሚድያ አዋርድ ልዩ ተሸላሚዋ መታሰቢያ ደረጀ

ተወዳጅ ሚድያ ባለሙያዎች  ተወዳድረው ሲያሸንፉ የሰዎቹን ማንነትና ምን ሠርተው ተሸለሙ? የሚለውን ሲያስተዋውቅ እንደነበር ይታወቃል።

ትናንት ህዳር 25 2018 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል  በተካሄደው የአፍሪካ ሚድያ አዋርድ መርሀ-ግብር መታሰቢያ ደረጀ ከኢቢሲ ልዩ ተሸላሚ ነበረች።
  የመታሰቢያን ሙያዊ ማንነት በአጭሩ እናስተዋውቃችሁ። ዕዝራ እጅጉ እንደሚከተለው ሰንዶታል።

መታሰቢያ ደረጀ አባተ የትውልድ ቦታዋ አዲስ አበባ መካኒሳ ነው።የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን እስከ 10 ዶን ቦስኮ ካቶሊክ ት/ቤት ተምራለች።
11ኛ- እና 12 ክፍልንም ቅድስተ-ማርያም ካቶሊክ ት/ቤት ተከታትላለች።

የመጀመሪያ ዲግሪዋን ሰመራ ዩኒቨርሲቲ  በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያገኘች ሲሆን ትምህርቷንም በመቀጠል ሁለተኛ ዲግሪዋን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋዜጠኝነት ለማግኘት በቅታለች።

በሚድያ ሥራ ከኤፍ ኤም  አዲስ 97.1 አንስቶ 13 ዓመት የዘለቀች ሲሆን ለሙያውም ከፍተኛ አክብሮት እንዳላት ትናገራለች።

ቲቪ ከገባች በኃላም ፕሮግራም/ዶክመንተሪ በመሥራት ልዩ አሻራ ማሳረፍ ችላለች።
በአሁኑ ሰዓት በኢቢሲ የዜና ከፍተኛ ኤዲተር፣ አዘጋጅና አንባቢ በመሆን እያገለገለች ትገኛለች።

መታሰቢያ በልጅነቷ  በጣም ዓይንአፋር ነበረች። ያ ተፅዕኖ ያሳድርባት ስለነበር ጋዜጠኛ የመሆን ሀሳብ አልነበራትም። ነገር ግን በጣም መፃፍ ትወድ ነበር። እና ሀሳቧን ወረቀት ላይ ታሰፍር ነበር። እያደገች ስትሄድ ከሰዎች ጋር ያላት ተግባቦት እየጨመረ ሲሄድ  አቀራረብ ላይ የበለጠ እየተካነች መጣች።  መታሰቢያ ስትናገር ” ይህም የንግግር ችሎታዬን እንዳሳድግ አድርጎኛል።”ትላለች።

“ሥነ ፅሁፍ በጣም እወድ ነበር ሀይስኩል እያለሁ። ከሚያዝናኑኝ ነገሮች አንዱ ግጥም መፃፍ ነበር። ዩኒቨርስቲ ሳለሁም ክለብ ዲል አርት የሚል የሥነ-ፅሁፍ ስብስብ አባል በመሆን ግጥም አቀርብ ነበር። ” በማለት ወደ ኃላ ተመልሳ ትዝታዋን ታወጋለች።

መታሰቢያ ዜናን የተቀላቀለችው ኤዲተር ሆና ነው ። የተለያዩ አጋጣሚዎች ላይ  ዜና ትሠራለች።
ኤፍ ኤም 97.1 ላይ” የጥበብ ማዕድ” እና “አዲስ ውበት” የሚሉ ፕሮግራሞች ታዘጋጅ ነበር።

የኢትዮጵያ አርታኢያን ማህበር አባል የሆነችው መታሰቢያ የአፍሪካ ሚድያ አዋርድ ውድድሩን እንዳወጣ ወዲያው አይታ ሥራዎቿን እንደላከች ትናገራለች ።
በማሸነፏም ደስተኛ መሆኗን ገልጻለች።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *