ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን፣ መዝገበ-አእምሮ (የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ) ፕሮጀክቱ ለአገር የሠሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ታሪክ በዲጂታል ሚድያዎች፣ በመጽሐፍ፣ በድምፅ ትረካና በሌሎችም መንገዶች እየቀረበ ይገኛል። በተለይ ጉግል ላይ ታሪካቸው ሲፈለግ የማይገኝ ሰዎች አሁን የሙያ አበርክቷቸው በቀላሉ ኢንተርኔት ላይ በግልፅ ተቀምጧል።
ባለፉት 4 ዓመት ከ 5 ወር ጊዜ ውስጥ የ423 ሰዎችን የሕይወትና የሥራ ታሪክ ለመሰነድ የቻልን ሲሆን 600 ገፅ ባላቸው ሁለት የተለያዩ መጽሐፎች ላይም ታሪኮቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድርገናል።
ከእነዚህ ውስጥ የሚድያ ሰዎችና የቴአትር ባለሙያዎች ይገኙበታል። አጠቃላይ 74 ከፍተኛ የሚድያ አመራሮች፣ ሚኒስትሮች፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የግል ሚድያ መሥራቾች፣ ዋና አዘጋጆች እና መካከለኛ አመራሮች ተካተዋል። 35 ያህሉ በዋና ሥራ አስፈጻሚ ደረጃ ያሉ ሲሆን የሁሉም ታሪክ በተሟላ ደረጃ ለመሰነድ ተችሏል። በተጨማሪም በሳይንስ፣ በመምህርነት፣ በምህንድስና እና በሌሎችም ዘርፎች ውስጥ ያሉ ሰዎችን ወደ አንባቢ እያመጣን እንዲታወቁ ጥናትና መረጃ ማድረግ ለሚሻም ተደራሽ ስናደርግ ቆይተናል።
የእነዚህን ሰዎች ታሪክ ሰንዶ ለአንባቢ ተደራሽ ማድረግ ፈታኝ ቢሆንም አሳክተነዋል። በዚህ ተግባራችንም ተጠናክረን እንቀጥላለን።
አሁን በዚህ ጽሑፍ ታሪኳን የሰነድነው ደራሲ ውድአላት ገዳሙ በሥነ ጽሑፍ እና በኮምዩኒኬሽን የራሷን አሻራ ያኖረች ናት። ከሰሞኑ የእድሜ ደመራ የተሰኘ በህይወት ታሪኳ ላይ ትኩረቱን ያደረገ መጽሐፍ ሊወጣ እየተቃረበ ነው። የቅድመ ግዤ የቻሌንጅ መርሀ ግብሩም በተወዳጅ ሚድያ አማካይነት እየተከናወነም እንደሆነ ይታወቃል። ውድአላት ገዳሙ ከልጅነት ጀምሮ እስከአሁን በምን አይነት መንገድ እንዳለፈች ከትበነዋል። ባለታሪኳን በማስፈቀድ ፣ የተዘጋጀውንም ፅሑፍ አይታ ማረጋገጫ እንድትሰጥ በማድረግ ታሪኳን ሰንደነዋል።እዝራ እጅጉ እንደሚከተለው ያቀርበዋል።
ከትናንት እስከ ዛሬ፣ በስኬት የረሰረሰች ሕይወት፡-
ትውልድ እና የቤተሰብ ሁኔታ
ደራሲ ውድአላት ገዳሙ፣ በድሮው የጎጃም ጠቅላይ ግዛት፣ በብቸና አውራጃ፣ በእነማይ ወረዳ፣ ልዩ ስሟ ቻክ በምትባል የገጠር መንደር፣ የካቲት 16 ቀን 1952 ዓ.ም. ተወለደች፡፡ ለወላጆቿ ስድስተኛ ልጅ ስትሆን፣ እናቷ ወይዘሮ ዘውዲቱ መኮንን፣ አባቷ ሊቀ ጠበብት ገዳሙ ተሻለ ይባሉ ነበር፡፡ አባቷ ሊቀ ጠበብት ገዳሙ የቤተክህነት ትምህርት የተማሩ በመሆናቸው፣ በታላቁ የብቸና ጊዮርጊስ ደብር በሊቀ ጠበብትነት ማዕረግ የቤተክርስቲያኑ ሹምና አገልጋይ የነበሩ ሲሆኑ፣ የብቸና ከተማ ማዘጋጃ ቤት የገንዘብ ቤት ሹም/በጅሮንድ ሆነው እስከዕለተ ሞታቸው ድረስ በመንግሥት ሠራተኛነት አገልግለዋል፡፡ በጊዜው ጥሩ አዳሪ ከነበረ ቤተሰብ የተገኘችው ውድአላት፣ የሕጻንነት ጊዜዋ በመልካም ሁኔታ ቢገነባም፣ ገና በልጅነቷ አባቷን በሞት ስላጣች ያደገችው “እርቦ” ተብሎ ከሚጠራ ከመሬት ባለቤትነት ከሚገኝ ሀብት፣ ከጓሮ ከሚገኝ የባሕር ዛፍና ጌሾ ሽያጭና ከሟች አባቷ ከተገኘ የጡረታ ገንዘብ ነው፡፡
የልጅነት ጊዜ
የሕፃንነት ጊዜዋን ያሳለፈችው በእናቷና በዙሪያዋ በሚገኝ ቤተሰብ እንክብካቤ ሲሆን ዕድሜዋ ለትምህርት እንደደረሰ፣ በትውልድ መንደሯ አቅራቢያ በሚገኘው በታላቁ ራስ ኃይሉ ዮሴዴቅ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብታ፣ በተለይ እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ ከቤተሰቧ ጉያ ሳትርቅ፣ እዚያው በትውልድ አካባቢዋ ተምራለች፡፡ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትማር በነበረችበት ጊዜ፣ በትምህርት ቤቱ ይካሄድ በነበረው የክርክር፣ የተውኔትና የሥነ ጽሑፍ ክበባት ውስጥ በመቀላቀል በተለይ በሥነ ግጥም ውድድር በሰንደቅ ዓላማ የአከባበር ሥነ ሥርዓት ላይ የልጅነት ግጥሞቿን በማቅረብ በመምህሮቿና በወላጆች ዘንድ “ወሸው” በመባል “ጭብጨባ” የሥነ ግጥም ሙከራዋን ያበለጸገላት ውጤታማ ታዳጊ ነበረች፡፡
ስፖርተኛዋ ውድአላት
ውድአላት፣ በተማሪዎች የስፖርት ውድድር በተለይም በአንድ እና በሁለት መቶ ሜትሮች ሩጫ፣ በእርዝመት ዝላይ እና በሲሊንግ ቦል ውርወራ፣ ትምህርት ቤቷን ወረዳዋንና አውራጃዋን በመወከል በምታስመዘግበው ውጤት በጠቅላይ ግዛቱ የሽልማት ሠንጠረዥ ውስጥ ስማቸውን ለማስጠራት የቻለች ንቁ ስፖርተኛ ተማሪ ነበረች፡፡ የስምንተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በጥሩ ውጤት በማለፍ በወቅቱ በትምህርትና ሥነ ጥበብ ሚኒስቴር አማካኝነት ከመላ ሀገሪቱ ከተመረጡ ጥቂት ተማሪዎች ጋር አዲስ አበባ ንግድ ሥራ ትምህርት ቤት ገብታ ለመማር የሚያስችላት ነጻ የትምህርት ዕድል ገጠማት፡፡ የኾኖ ኾኖ ለአንዲት አዲስ መጤ የገጠር ልጃገረድ፣ ቢያንስ በትምህርት ቤቱ አካባቢ የሚገኝ የተመቻቸ መጠጊያ ያስፈልግ ስለነበር፣ ወደ አዲስ አበባ መጥታ ለመማር ሳይቻላት ይቀራል፡፡ ይህ አጋጣሚ በልጅነት አእምሮዋ ውስጥ ቁጭትን፣ ጸጸትንና እልኽን ጭሮ እየታገላት፣ የዘጠነኛና የአሥረኛ ክፍልን ለመማር ወደ ደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሄዳ በመመዝብ ትምህርቷን ቀጠለች፡፡
ጉዞ ወደ መምህርነት
ውድአላት ቀድማ ለምትወዳቸው እናቷ፣ ለታናናሾቿና ለቤተሰቧ ቀድማ ለመድረስ በነበራት ፍላጎት፣ በጅማ መምህራን ማሠልጠኛ ተቋም ገብታ በመሠልጠን፣ በመምህርነት ሙያ በዲፕሎማ ተመርቃ፣ መልካም ሥነ ምግባር ያላቸው ዜጎች እንዲወጡ በነበራት ቀናዒ አስተሳሰብ፣ ትኩስ ጉልበቷንና መረቅ ዕውቀቷን ለስስት አፍስሳለች፡፡ ገና በለጋ ዕድሜዋ ከመምህር የሐሳቡ ያሬድ ትዕዛዙ ጋር በጋብቻ ተጣምራ፣ የሁለት ሴቶችና የአንድ ወንድ ልጅ በድምሩ የሦስት ልጆች እናት እንዲሁም የሰባት ሕፃናት አያት በመሆን፣ የተሳካላት ባለትዳር ለመሆን የበቃች ደራሲት ናት፡፡ ደራሲት ውድአላት፣ የሥራ ሕይወቷን በጀመረችበት የመምህርነት ሙያ በተለያዩ የገጠር ትምህርት ቤቶች በበቅሎና በፈረስ ጀርባ በመዘዋወር፣ ከሰባት ዓመታት በላይ የፊደል አዝመራን ዘርታ መልካም ዜጎችን ለምትወዳት ሀገሯ ለማፍራት ችላለች፡፡
ገና በለጋነቷ ያገኘችው በከፍተኛ ተቋም ገባታ የመማር ዕድል የተጨናገፈባት ደራሲዋ፣ በባሕር ዳር መምህራን ኮሌጅ በማታው የትምህርት መርሐ ግብር በእንግሊዝኛ ቋንቋ ገብቶ በመማር፣ ኋላም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ በውጭ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ ተምራ ለማጠናቀቅ በቅታለች፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ (በ 2018 ዓ.ም.) በፎክሎርና በባህል ጥናት የሦስተኛ ዲግሪዋን በመሥራት ላይ ትገኛለች፡፡ በሥራ ሕይወቷ በማስተማር ሙያ ለሰባት ዓመታት ካገለገለች በኋላ በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች በመቀጠር፣ በሥነ ጽሑፍ ኤክስፐርትነት፣ በጽሑፍ ኤዲተርነት፣ በመጽሔት አዘጋጅነት፣ በኮሚዩኒኬሽን
አገልግሎት ኃላፊነት በመመደብ የተጣለባትን ኃላፊነት በብቃትና በትጋት ስታከናውን ቆይታለች፡፡
የሥነ ጽሑፍ እና የሚድያ አሻራ
ደራሲ ውድአላት ገዳሙ፣ ከአንደኛ ደራጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ በነበራት የሥነ ጽሑፍ ተሰጥዖና ፍላጎት፣ በወጣቶችና በሴቶች ማኅበራት መድረኮች በግጥሞችና በልዩ ልዩ መጣጥፎች ሰፊ ተሳትፎ ስታደርግ ከመቆየቷም በተጨማሪ፣ ነበር፡፡ ይኸንኑ ተሰጥኦዋን ለማዳበር እንዲያስችላት በትምህርት ሚኒስቴር አማካኝነት ለስድስት ወራት ሥልጠና ወደ ቀድሞዋ ምሥራቅ ጀርመን በሚገኘውና “ጌራ ካውንቲ” ተብሎ በሚታወቀው ክፍለ ግዛት፣ሩዶልሽታት ከተማ ውስጥ በሚገኘው የሮዛ ሉግዝምበርግ የፖለቲካ ትምህርት ቤት፣ በሶሻሊስት ርዕዮተ ዓለም የፍልስፍና ትምህርት ተከታትላ ተመልሳለች፡፡
ደራሲ ውድአላት፣ በነበራት የሥነ ጽሑፍ ተሰጥዖና ባከማቸችው በዕውቀት የታገዘ ችሎታ ሳቢያ፣ በወቅቱ በተደረሰበት የአዲስ አስተሳሰብ አቅጣጫ፣ ሀገርን ከድኅነት እንዲሁም ወገንን ከማሃይምነት ለማላቀቅ በነበረው ገዥ አስተሳሰብ ተስባ፣ በኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (ኢሠፓ) ልሣን ለነበረው “ሠርቶ አደር” በጋዜጠኝነት በመቀጠር፣ በመጀመሪያ የጎጃም ክፍለ ሀገር የጋዜጣው ሪፖርተር እና አስተባባሪ ሆና በመሾም እየተዘዋወረች በክልሉ የሚገኙትን ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሀብቶች ዘግቦ በማጠናቀር አስተዋውቃች፤ የኃላፊነት ድርሻዋን በብቃት መርታለች፡፡
በሥራ ቅያሬ ወደ አዲስ አበባ ከተዛወረች በኋላም ዐራት ኪሎ በሚገኘው የኢሠፓ ማእከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት በመመደብ፣ የጋዜጣው የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ በመሆን በሥራ አፈጻጸሟ በተመስጋኝነት ሠርታለች፡፡ በሀገሪቱ የተከሰተውን የመንግሥት ለውጥ ተከትሎ በተፈጠረው የሥራ መሸጋሸግ፣ ወደቀድሞው ቤቷ፣ ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ተመድባ የበአዲስ አበባ
ከተማ ትምህርት ቢሮ ከ1984 እስከ 1993 ዓ.ም. ድረስ በመምህርነትና በሥነ ጽሑፍ ኤክስፐርትነት፣ በተለይ ‹‹ዕውቀት›› ለተሰኘው የቢሮው ልሳን መጽሔት ም/አዘጋጅ በመሆን አገልግላለች፡፡ ከዚያም በጋዜጣ በወጣ ማስታወቂያ መሠረት በማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጄንሲ፣
ለሥነ ጽሑፍ ኤክስፐርነት ተወዳድራ ስለተሳካላት፣ በዚሁ መ/ቤት በመጀመሪያ የሥነ ጽሑፍ ኤክስፐርት፣ ቀጥሎ የሕዝብ ግንኙነትና የመረጃ ሥርጭት መምሪያ ኃላፊ በመጨረሻም የጡረታ ዋስትናዋን እስካስረከበችበት ቅርብ ጊዜ ድረስ፣ የዲፓርትመንቱ ዳይሬክተር በመሆን፣ አገልግላለች፡፡
በግል ድርጅቶችም በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ እና በቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ሆና በመመደብ የሠራች ሲሆን፣ ደራሲዋ በመንግሥት መሥሪያ ቤትም ሆነ በግል ድርጅቶች ውስጥ በሠራችባቸው የሥራ ቦታዎች ሁሉ፣ በኃላፊነት ታስተባብራቸው ለነበሩ ወጣት የሥራ ባልደረቦቿ የሕይወት፣ የሥራና ወደ ተለያዩ የውጭ ሀገራት ለምሳሌ በምሥራቅና በምዕራብ ጀርመን፣ በአውስትራሊያ፣ በኖርዌ፣ በእንግሊዝ፣ በአሜሪካ፣ በጣሊያን፣ በዱባይ፣ በኬንያ፣ በደቡብ አፍሪካ፣ በካሜሮን፣ በኡጋንዳ፣ በቱርክ፣ በሲንጋፖር…,ሄዳ በመ/ቤት፣ በድርጅቶችና በግልም ጭምር ሀገሯን በመወከልና በመሳተፍ ያካበተችውን ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ሳይቀር እያካፈለች፣ እነርሱ ከእርሷ የተሻሉ አምራች ባለሙዎችና የመልካም ሥነ ምግባር ተገዥዎች ሆነው እንዲቀረጹ አርአያነት ያለው ተግባር ስታከናውን ኖራለች፡፡
በአጠቃይ እግረ መንገዷን በምትሄድባቸው ሀገራት በተዘጋጁ መድረኮች በመገኘት ለዐዋቂዎችና ለሕፃናት ያዘጋጀቻቸውን መጽሐፎችና ሌሎች የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች፣
በማስተዋወቅ ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያዊነት ክብር ንግግር አድርጋለች፣ ግጥሞቿንም አቅርባለች፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በጋራና በግል የተሠሩ አጫጭር ልቦ’ለዶቿን፣ ግጥሞቿን፣ ለጋዜጣ የዋሉ የተለያዩ መጣጥፎቿን የጉዞ ማስታወሻዎቿን ወዘተ…በማቀናበር ለንባብና ለኅትመት አብቅታለች፡፡
ለምሳሌም፣ያህል፡–
- ብድሯን ያልከፈለች ወፍ፡- በ 2001 ዓ.ም. (ሁለት ጊዜ የታተመ) ብድር፣ከፋዮቹ፣ወፎች፡-በ2005፣ዓ.ም.፣በአማርኛ፣ተጽፎ፣፣በኦሮምኛና፣በትግርኛ የተተረጐመ፣
- ወርቃማዋ፣ድኩላ፡-፣በአማርኛ፣ተጽፎ፣፣በ 2005ዓ.ም. በኦሮምኛና በትግርኛ ቋንቋ የተተረጐመ፣
- ጓደኛሞቹ፡- 2005 ዓ.ም፣ በዚሁ ዓመት
በባሕር፣ዳር ዩኒቨርሲቲ ለሽልማት የበቃ፣ - ደንሽ ሳሮን ደንሽ››፡- በ 2007 ዓ.ም. በጀርመን የባሕል ተቋም አስተባባሪነት
በአማርኛና፣በጀርመንኛ ቋንቋ በጋራ፣ - የዜብራ፣ተረቶች፣ቁጥር፣፩፡- በ 2008 ዓ.ም.፣
- የዜብራ፣ተረቶች፣ቁጥር፣2፡-፣በ2009፣ዓ.ም በግል አሳትማ ለሕፃናት ንባብ አበርክታለች፡፡ በዚህም መምኅርነትን፣ የእናትነትን፣
የአያትነትንና የዜግነትን ድርሻ ተወጥታለች፡፡ - እናትና ልጅ፡-፣ የግጥም መድበል በግል) በ 1996፣ዓ.ም.፣ ስደተኛ ግጥሞች የግጥም መድበል፣2003 ዓ.ም.
ዕጣ፡- የአጫጭር ልቦʼለዶች ስብስብ፣ በ 1995 ዓ.ም. ከሌሎች ጸሐፊዎች ጋር፣
የዘመን፣ቀለማት፡-የግጥም፣መድበል፣በኢትዮጵያ፣ደራስያን፣ማኅበር
በ 1999፣ዓ.ም.፣ከሌሎች ጸሐፊዎች ጋር፣ - ዜማ ብዕር ቁጥር 1፡-የግጥም ስብስብ በ 2003 ዓ.ም. ከሌሎች ጸሐፊዎች ጋር፣
- ዜማ ብዕር ቁጥር 2፡- የአጫጭር ልቦʼለዶች ስብስብ በ2003 ዓ.ም. ከሌሎች ጋር፣
ከዚህ በተጨማሪም በርካታ የመሥሪያ ቤት ልሳን የሆኑ መጽሔቶችን በአማርኛና በእንግሊዝኛ ስታዘጋጅ ቆይታለች፡፡ ደራሲዋ፣ በተለይ መምህርት በነበረችበት ጊዜ በተለይ ተማሪዎቿን፣ የትምህርት ቤት ማኅበረሰቡንና ወላጆችን በማመካከር፣ በትምህርት ጉዳይ ላይ ተገቢውን ሚና እንዲጫወቱ በማነሳሳት፣ በርካታ የተውኔትና የመዝሙር ጽሑፎችን እያዘጋጀች፣ የየአካባቢው ማኅበረሰብ እንዲማርባቸውና የትምህርቱን ሥራ እንዲያግዝ ስትሠራ ቆይታለች፡፡ ከሁሉም በላይ በሥነ ጽሑፍ ሥራዎቿ ይበልጥ ትኩረት የአደረገችው ሕፃናት በመልካም ሥነ ምግባር እንዲቀረጹና በበጎ አስተሳሰብና አመለካከት እንዲገነቡ ያበረከተችው አስተዋጽዖ ነው፡፡ የሕፃናትን አዕምሮ በማጎልመስ በኩል፣ እንደ ተጨማሪ የሚጠቀሱ ሌሎችም የሥነ ጽሑፍ ሥራዎችን ያበረከተች ሲሆን፣ ለአብነት ያህልም በትምህርት
ሚኒስቴር አስተባባሪነት የሥነ ምግባርና የሥነ ዜጋ መጽሐፍ ከ5ኛ 8ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች ማስተማሪያ በሚሰናዳበት ወቅት፣ መጽሐፉን እንዲያዘጋጁ በሀገር ደረጃ ከተመረጡ ባለሙዎች አንዷ ነበረች፡፡ በዚህ መጽሐፍ አማካኝነት፣
ሕፃናትና ታዳጊዎች ስለ ጠንካራ የሥራ ባሕል የተስተካከለ ፅንሰ ሐሳብ እንዲኖራቸው የሚያበቃ፣ጽሑፍ፣አስተዋፅዖ፣በማድረግ፣የበኩሏን፣ድርሻ ተወጥታለች፡፡
ከ1993- 1996 ፣ዓ.ም፣ድረስ ከሴ አጨዳ፣ ሚሻ ሚሾ፣ ለእናት ዋጋ አነሳት፣ ሰው ጠላሁ፣ የጡት ካንሰር ምንነት (ትርጉም)፣ ቁጠባን ከምን
እንጀምር? ቅዳም ሽሁር… እና ሌሎች በርካታ መጣጥፎችን በማዘጋጀት፣ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ፣ በባሕልና በሌሎች ዓምዶች ላይ በማሳተም ለንባብ አብቅታለች፡፡ በሌላም በኩል በብዕር እና በዓለም ስሟ ተጠቅማ የዜማ
ደርሶ መልስ..እና የተለያዩ የጉዞ ማስታወሻዎችን በአዲስ ዘመንና በዕለታዊ አዲስ ጋዜጦች፣ተከታታይ፣ዕትሞች፣ላይ ፣ሲታተሙላት
ቆይተዋል፡፡ ‹ሞተር ጠጋኙ መነኩሴ፣ ከገረገራ እስከ ዋሸራ… በሚል ርዕስ በቀድሞው የሠርቶ፣አደር፣ጋዜጣ፣ላይ፣ተከታታይ የጉዞ ማስታወሻ ጽሑፎችን፣ ስለ ዋሸራ የቅኔ ትምህርት ቤት ታሪክ፣ ስለ ጥበበኛዋ ባለቅኔ እማሆይ ገላነሽ ሀዲስና ስለሌሎች
የቅኔ ሊቆች በርካታ ጽሑፎችን ለንባብ አብቅታለች፡፡
ልዩ ልዩ አስተዋጽኦ
በሕይወት ጉዞዋ በርካታ ገጠመኞች ቢኖሯትም አብልጣ የምታወሳው ግን፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣እየተማረች፣በነበረችበት፣ጊዜ፣የገጠማትን ቤተሰባዊ መልካም ገጠመኝ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያና የሁለተኛ ዲግሪዋን በሁለት የተለያየ ጊዜያቶች በያዘችበት ወቅት፣ ከመጀመሪያ ሴት ልጇ ጋር በአንድ፣ቀንና፣ በአንድ አዳራሽ መመረቋ ነበር፡፡ ይህ ከፍተኛ ደስታን የፈጠረላት ቤተሰባዊ አጋጣሚ እንደነበር ታስታውሳለች፡፡ እናትና፣ልጅ፣በአንድነት የመመረቅ አጋጣሚ፣ በሀገራችን እጅግ አልፎ አልፎ የሚከሰት በመሆኑ፣ በወቅቱ ለብዙ ቤተሰቦች እንደመልካም አርአያና ተምሳሌት ሆኖ
ታይቷል፡፡ እናትና ልጅ በሚል የግጥም መድብሏን የሰየመችውም በዚሁ የቤተሰብ ገጠመኝ የተነሳ እንደሆነ ታስታውሳለች፡፡ በ 1997 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበርን፣በአዲስ፣አደረጃጀት ለማጠናከር በተደረገው ጥረት፣ በመጀመሪያው ጠቅላላ ጉባኤ፣ የአደራጅ ኮሚቴ አባል በመሆን ማኅበሩን በጥንካሬ የሚመሩ አባላት ወደ አመራር እንዲመጡ የበኩሏን አስተዋፅዖ አድርጋለች፡፡
በአባልነቷ ንቁ ተሳትፎ ከማድረጓ በተጨማሪ የማኅበሩ የመማክርት ጉባኤ አባል፣በመሆን፣፣አገልግላለች፡፡፣የኢትዮጵያ ሴት፣ደራስያት ክበብ አባል ሆና በጽሑፍ አርታዒነትና በምክትል ፕሬዝደንትነት፣ በኋላም በፕሬዝደንትነት የመራች ሲሆን፤ የዜማ ብዕር፣ ኢትዮጵያ፣ ሴት የሥነ ጽሑፍ ማኅበር መሥራች በመሆን፣ ከምሥረታው ጀምራ ለነበሩት ስድስት ተከታታይ ዓመታት በምክትል ፕሬዝደንትነት አገልግላለች፡፡በመንግሥትና በድርጅቶች የሚዘጋጁ የተለያዩ የሥነ ጽሑፍ ውድድሮች፣ በተለይም የአዲስ አበባ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ሚሊኒየም አከባበር፣
ለከተማው ሕዝብ ባዘጋጀው የኪነ ጥበባት መሰናዶ፣ እንዲሁም ዳሸን ቢራ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያዘጋጀውን የሥነ ጽሑፍ ውድድር እና ሌሎችንም በመሀል ዳኝነት መርታለች፡፡ በርካታ የምስጋና ወረቀቶችንም ወስዳለች፡፡
የቡና ባንክ በ2003 ዓ.ም መሥራች ጉባኤውን ባደረገ ጊዜ፣ ባንኩን በቦርድ አባልነት እንዲመሩ ከተመረጡ የቦርድ አባላት መካከል አንዷ ስትሆን፣ በሜሪ ጆይ የሕፃናትና የአረጋውያን መርጃ ድርጅት ባደረገችው ከፍተኛ
አስተዋጽዖ፣ የማኅበሩ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር በመሆን፣ በኢትዮጵያ የማቲዎስ ወንዱ የካንሰር ሶሳይቲ እና በመሳሰሉት በጎ አድራጎት ድርጅቶች በመሳተፍ፣ በዕውቀቷና በሙያዋ ወገኖቿን በማገልገል ላይ ትገኛለች፡፡
ጥበብ የአሳየቻትን ፈር ተከትላ፣ አቅሟ በፈቀደላት መጠን፣ የመዝሙር፣የዘፈን እና የለቅሶና የኀዘን እንጉርጉሮ ግጥሞችን በማሰናዳት፣ እገዛዋን ለጠየቁ ድርጅቶችና ግለሰቦች ተገቢውን ድጋፍ ትሰጣለች፡፡ በልጅነቷ የምታስታውሳቸው የአበባየሁሽ ዘፈኖች ከነባር ግጥሞቻቸውና ባሕላዊ
ለዛቸው ጋር ለትውልድ እንዲተላለፉ ባ’ላት ጠንካራ እምነት፣ የእንቁጣጣሽን ዘፈን ከነሙሉ ግጥሙ በማዘጋጀት፣ በራሷ ድምፅ ተቀርፆበመገናኛ ብዙኀን እንዲሰራጭና ለትውልድ በቅርስነት እንዲቀመጥ ሁነኛ አስተዋጽዖ አበርክታለች፡፡
ውድአላት እንደ ደራሲነቷ ማኅበረሰቡን ማወቅና በጉዳዮቹም መሳተፍ እንዲሁም
ነፃ አገልግሎት መስጠት ግዴታዋ መሆኑን በመገንዘብ፣ የጣና ሐይቅን ከእንቦጭ አረም ለመከላከል፣ ዓባይ-ጣና ብዝኃ ሕይወት፣ ባሕል ጥበቃና
አካባቢ አያያዝ የበጎ አድራጎት ማኅበርን በመመሥርትና በሥራ አስኪያጅነት በመሾም ድርጅቱ ለተቋቋመለት ዓላማ እንዲበቃ በማስተባበር መርታለች፡፡ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የሚደረገውን
ሀገር አቀፍ ጥረት ለማገዝ፣ ከ 2006 ዓ.ም ጀምራ በምትኖርበት ሠፈር፣ ዓላማዋን ከደገፉ ፈቃደኞች ጋር በመሆን፣ ዘወትር በማለዳ ወደ አውራ
መንገድ እየወጣች፣ ተላላፊው ሕዝብ ከትራፊክ አደጋ እንዲጠነቀቅ በመምከርና በማስተማር፣ ለሌሎች ምሳሌነት ያለው ተግባር በመፈጸም ላይ ናት፡፡
የትራፊክ አደጋን የመከላከል ልማድ ወደ ሕፃናትና ታዳጊዎች እንዲሰርፅባ’ላት ጽኑ ፍላጎት፣ ለሕፃናት የምትጽፋቸውን የተረት መጽሐፎች ስያሜ፣ በዚሁ ዙሪያ በማድረግ፣ ልጆች ከለጋ ዕድሜያቸው ጀምሮ ስለትራፊክ አደጋ ግንዛቤ ኖሯቸው፣ ራሳቸውንና ማኅበረሰባቸውን እንዲጠብቁ ጥራለች፡፡ ይህን ሐሳብ ተመርኩዛ ከአዘጋጀቻቸው መጽሐፎቿ መሐል፣ የዜብራ ተረቶች ቁጥር ፩ እና የዜብራ ተረቶች ቁጥር 2 የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ከላይ እንደተገለጸው ውድአላት በሥነ ጽሑፍና በተለያዩ ማኅበራዊ
ጉዳዮች ንቁና ትጉህ ተሳታፊ በመሆኗ በርካታ የምስጋና ሽልማቶችና ምስክር ወረቀቶችን አግኝታለች፡፡
ጥቂቶቹን ለማመላከት ያህል‹----
- ከቡና፣ባንክ፣ የረጅም ጊዜ የቦርድ አባልነት አገልግሎት የምስጋና ሰርቲፊኬት፣
- ከባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፡- የላቀ አስተዋጽዖ ዕውቅና ሰርቲፊኬት፣
- ከኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር፡- በ50 ዓመት የምሥረታ ክብረ በዓል ዓለም አቀፍ ጉባዔ ዝግጅት በኮሚቴ አባልነት ለተደረገ የላቀ ድጋፍ የምስክር ወረቀት፣
- ከሜሪ ጆይ የሕፃናትና አረጋውያን መርጃ ድርጅት፡- የበጎ ፈቃድ አምባሳደርነት
ሰርቲፊኬት፣ - ከዳሸን ቢራ፡- የኪነ ጥበባት ውድድር ለተደረገ የዳኝነት አገልግሎት የተሰጠ የምስጋና፣ሰርቲፊኬት፣
- ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማኅበራት ፌዴሬሽን፡- የምስጋና የምስክር ወረቀት ይገኙበታል፡፡
ደራሲዋ ላለፉት 40 ዓመታት በመራችው የተረጋጋና የተደላደለ የትዳር፣ የሥራና የጥበብ ሕይወቷ፣ ባለቤቷ የአንበሳውን ድርሻ እንደተጫወተ በአድናቆት ታወሳለች፡፡ ገና በልጅነት ዕድሜዋ አባቷ በሞት ቢለዩዋትም፣ እናቷ በአነስተኛ የጡረታ አበል፣ ከመሬት ከሚሰበሰብ እህልና ከዛፍ ሽያጭ በሚያገኙት ገቢ በጥሩ ሁኔታ አድጋ ለቁም ነገር እንድትበቃ ደግሞ እናቷ ቀዳሚ ባለውለታዋ ናቸው፡፡ እናቷ ገና በወጣትነት ዕድሜያቸው ትዳራቸው በሞት ቢፈታም፣ እናቷ የእንጀራ አባት ግንባር ሳያሳዩዋት፣ እንደ ሰፈር ጓደኞቿ በሕፃንነት ለ-ያለዕድሜ ጋብቻ ሳትዳረግ፣
ትምህርቷን የማቋረጥ መጥፎ ዕጣ ሳያገኛት ትምህርቷን እስከ ዐሥረኛ ክፍል በማጠናቀቅ በመምህርነት ሙያ ሠልጥና ለተሻለ ደረጃ የበቃችው በእናቷ በወይዘሮ (በኋላ በእማሆይ) ዘውዲቱ መኮንን ጥንካሬና ብርታት እንደሆነ በጽኑ ታምናለች፡፡ ደራሲዋ በአሁኑ ወቅት ራሷን በዕውቀት ለመገንባትና ገና ከልጅነቷ ጀምራ በውስጧ ተቀብሮ የኖረውን የትምህርት ፍላጎትና ያደረ ቁጭቷን ለማርካት፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ በፎክሎርና በባህል ጥናት ዘርፍ፣ የሦስተኛ ዲግሪዋን፣በመሥራት፣ላይ፣ትገኛለች፡፡