የአክሊሉ ሀብተወልድ ታሪካዊ ንግግር

አክሊሉ ሀብተወልድ

አክሊሉ ሀብተወልድ ሀሙስ መጋቢት 15 1958 አ.ም ሀገሪቱን በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንደሚያገለግሉ ከተነገራቸው በኋላ መጋቢት 16 በነጋታው ዜናው ‹‹የኢትዮጵያ ድምጽ›› ጋዜጣ ላይ ታትሞ ወጣ፡፡ አክሊሉም ከ19 ቀን በኋላ ማለትም ማክሰኞ ሚያዝያ 4 1958 ከማታው በ2 ሰአት በራድዮ እና በቲቪ ንግግር አደረጉ፡፡ ካቢኔያቸውንም በይፋ አሳወቁ፡፡

አክሊሉ ሀብተወልድ በዛን እለት ለሀገራችን ህዝብ ያደረጉት ንግግር 7 ገጽ ወይም 22 ደቂቃ የፈጀ ንግግር ነበር፡፡ ይህንን ንግግር ድምጹን ራሱን በሚገባ ስላዳመጥኩት ሙሉውን በቅርቡ ታደምጣላችሁ፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ድምጽ›› ጋዜጣ ላይ ሙሉ ንግግራቸው ያለ በመሆኑ በመጠኑ ትመለከቱት ዘንድ እነሆ ብያለሁ፡፡ አክሊሉ በንግግራቸው ለስራ መነሳት እንደሚያስፈልግ ፤ አንድ ተሁኖ ከተሰራ ሀገርን ማበልጸግ ቀላል እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ ንግግራቸው በዚህ ሊንክ ውስጥ ስላለ ጥሞና ሰጥቶ ማድመጥ ይቻላል፡፡ https://www.facebook.com/achamyeleh.tamiru.3/videos/1764735390215069/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *