ክብር ለ5ቱ ጠቅላይ ሚኒስትሮች

ትሁቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተወልድ በመጋቢት 1958 ማለትም የዛሬ 52 አመት በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲሾሙ ፣ እስከ ዛሬ ጠዋት ድረስ ሀገራችንን የመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ከተወለዱ 8ወር ሆኖአቸው ነበር፡፡ ደግሞ ልጅ እንዳልካቸው መኮንን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲሾሙ ያሁኑ የሀገራችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ገና ሊወለዱ 18 ወራት ይቀራቸው ነበር፡፡

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በ1987 ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሆኑ ያሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶክተር አቢይ አሕመድ የ19 አመት ታዳጊ ነበሩ፡፡ ከላይ ልጠቅሳቸው የሞከርኩት ጠቅላይ ሚኒስትሮች በሀገራችን ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ያላቸው ናቸው፡፡

5ቱም የትውልድ ስፍራቸው የተለያየ ነው፡፡ 5ቱም የራሳቸው መለያ አላቸው፡፡ 5ቱም የላቀ አእምሮ ባለቤት ናቸው፡፡ 5ቱም ሀገራቸውን ይወዳሉ፡፡ 5ቱም እስከ ማስተርስ ደረጃ ተምረዋል፡፡ 5ቱም አንባቢ ናቸው፡፡ 5ቱም በአንድ ላይ ሆነው አያውቁም፤ ነገር ግን በአንድ ጉዳይ ይስማማሉ፡፡ ወይም አንድ የጋራ ነጥብ አላቸው፡፡ ኢትዮጵያ …… ምንም በተለያየ ዘመን ቢወለዱ ….. ምንም በራሳቸው መነገድ ተጉዘው ታሪክ ላይ የተጻፉ ቢሆኑ ሊከበሩ ሊወደሱ ይገባቸዋል፡፡ ክብር ለ5ቱ ጠቅላይ ሚኒስትሮች፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *