ነገሩ ከሆነ 52 አመት አለፈው፡፡ አርብ መጋቢት 16 1958 ፡፡ ቀዳማዊ ሀይለስላሴ አዲስ የስራ አመራር መዘርጋት አለበት ብለው ጸሀፌ- ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው ሾሙ፡፡ በዛን ወቅት አክሊሉ የ54 አመት ሰው ነበሩ፡፡
አቶ ከበደ አኒሳ በዋና አዘጋጅነት የሰሩበት የኢትዮጵያ ድምጽ ጋዜጣ የአክሊሉን ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን በፊት ለፊት ገጹ ላይ አሰፈረው፡፡ በዛን ወቅት የኢትዮጵያ ድምጽ ጋዜጣ ዋጋው 5ሳንቲም ነበር፡፡
የጋዜጣው መሪ መፈክር ደግሞ ‹‹ኢትዮጵያ ትቅደም›› ፡፡ አስቡት ዘመኑ የደርግ ሳይሆን የጃንሆይ ነበር፡፡ አርብ መጋቢት 16 1958 ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆኑ የተነገራቸው አክሊሉ ለታላቅ አደራ መሰናዳታቸውን ቀጠሉ፡፡
ካቢኔያቸውንም ማደራጀታቸውን ቀጠሉ፡፡ ቀደም ሲል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ነበሩና አሁን ስልጣኑ ተሟልቶ ሲሰጣቸው በበጎ መልኩ ሀገርን ለመርዳት ታጥቀው ተነሱ፡፡