ሰናይት በዙ Senait Bezu

ሰናይት በዙ እውቅና ተበረከተላቸው

ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ለሽልማት የቀረቡ ባለሙያዎችን የሙያ ታሪክ ሲሰንድ እና ሲያስተዋውቅ እንደነበር ይታወቃል።ከዚህ ቀደም የበጎሰው፣ የአርአያ ሰው፣ የክብር ሽልማት፣ የሚድያ አዋርድ፣ የጷግሜ ሽልማት፣ የእንቁ ሴት ፣ ውድድሮች ላይ የቀረቡ ሰዎችን ታሪክ ሠርተን ለትውልድ ተደራሽ ማድረጋችን ይታወቃል።

ተሸላሚዎች ምን ሰርተው ታወቁ ወይም ተሸለሙ? የሚለውን ሰው ማወቅ የሚሻ በመሆኑ እኛም ማስተዋወቃችንን እንቀጥላለን።

ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ፣ መዝገበ-አእምሮ ( የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ) ፕሮጀክቱ ለአገር የሠሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ታሪክ በዲጂታል ሚድያዎች ፣በመፅሀፍ፣በድምፅ ትረካና በሌሎችም መንገዶች እየቀረበ እንደሆነ ይታወቃል።በተለይ ጉግል ላይ ታሪካቸው ሲፈለግ የማይገኝ ሰዎች አሁን የሙያ አበርክቷቸው በቀላሉ ኢንተርኔት ላይ በግልፅ ተቀምጦ ይገኛል።

ባለፉት 4 ዓመት ከ 5 ወር ጊዜ ውስጥ የ423  ሰዎችን የሕይወትና የሥራ ታሪክ ለመሰነድ የቻልን ሲሆን 600 ገፅ ባላቸው ሁለት የተለያዩ መፅሐፎች ላይም ታሪኮቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድርገናል።

ከእነዚህ ውስጥ የሚድያ ሰዎችም፣ የቴአትር ባለሙያዎች  ይገኙበታል። አጠቃላይ 74 ከፍተኛ የሚድያ አመራሮች፣ሚኒስትሮች ፣ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የግል ሚድያ መሥራቾች፣ዋና አዘጋጆች እና መካከለኛ አመራሮች ተካተዋል። 35 ያህሉ በዋና ሥራ አስፈጻሚ ደረጃ ያሉ ሲሆን የሁሉም ታሪክ በተሟላ ደረጃ ለመሰነድ ተችሏል።በተጨማሪም በቱሪዝም፣ በሥራ ፈጠራ፣ በሳይንስ፣ በመምህርነት፣ በአገር አስተዳደር ፣በምህንድስና እና በሌሎችም ዘርፎች ውስጥ ያሉ ሰዎችን ወደ አንባቢ እያመጣን እንዲታወቁ ጥናትና መረጃ ማድረግ ለሚሻም ተደራሽ ስናደርግ ቆይተናል።

የእነዚህን  ሰዎች ታሪክ ሰንዶ ለአንባቢ ተደራሽ ማድረግ ፈታኝ ቢሆንም አሳክተነዋል። በዚህ ተግባራችንም ተጠናክረን እንቀጥላለን።

አሁን በዚህ ፅሑፍ ታሪካቸው የሚዳሰሰው ሥራ ፈጣሪ ወይዘሮ ሰናይት በዙ ይባላሉ። ታሪካቸውም በዕዝራ እጅጉ እንደሚከተለው ተሰንዷል።

ትውልድ እና ቤተሰብ

በታሪካዊቷ አዲስ አበባ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ ከእናታቸው ከወ/ሮ ወለተኪዳን ይርባሸ እና ከአባታቸው ከአቶ በዙ ፎንዜ ተወልደው ያደጉት ወ/ሮ ሰናይት፣ ለቤተሰባቸው ሰባተኛ ልጅ ሲሆኑ፣ በትዳር ህይወታቸውም የሁለት ሴቶች እና የሁለት ወንድ ልጆች አርአያ እናት ናቸው።

የትምህርት ጉዟቸው

በማርኬቲንግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን፣ በማኔጅመንት ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን፣ የሦስተኛ ዲግሪያቸውን በሆቴል ማኔጅመንት ከሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ተቋም (CTTI) የተቀበሉት የዛሬው «ኤልገል ሆቴል» በግንባታ ላይ በነበረበት ከፍተኛ የሥራ ጫና ወቅት ከጎንዮሽ ሥራ ጋር አብረው ታግለዋል።

ኢኮኖሚያዊ ማብቃት እና የስራ እድል

በአሁኑ ወቅት «ኤልገል ሆቴል እና ስፓ» ባለቤት እና ሥራ አስኪያጅ በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት ወ/ሮ ሰናይት፣ ሆቴሉ ከ240 በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል እንዲፈጠር አድርገዋል። ሆቴሉ በኮንስትራክሽን ላይ በነበረበት ጊዜ
አንዳችም የትምህርት ዝግጅት ወይም የሥራ ልምድ ያልነበራቸወን የቀን ሠራተኛ ሴቶች በመቅጠርና አስፈላጊውን ሙያዊ ስልጠና በመስጠት በኩሽና(Kichen)በደህንነት (Safety and Security) እና በቤተ-ጽዳት (housekeeping)ክፍሎች ውስጥ ወደ ታላቅ የኃላፊነት መደብ  አሸጋግረዋል ።ይህ ተግባራቸው ሴቶችን በኢኮኖሚ የማብቃት፣ ራስን የመቻል እና የክብር ባለቤት የማድረግ ጥልቅ ህልማቸው ታላቅ ማረጋገጫ ነው።
ማህበራዊ አመራር እና በጎ አድራጎት የንግድ ስኬታቸውን ሁልጊዜም ከህብረተሰብ አገልግሎት ጋር አጣምረው የሚጓዙት ወ/ሮ ሰናይት፣ የተለያዩ ማህበራዊ ኃላፊነቶችን በንቃት በመወጣት ላይ ይገኛሉ፦

·         በአዲስ አበባ ሮታሪ ክለብ (Rotary Club of Addis Ababa West) አባልነት
·         በሴቶች በንግድ ማህበር Association women in business (AWiB) አባልነት ተሳትፎ
·         በአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር የቦርድ አባልነት ተሳትፎ
·     
·         ተለይተው የታወቁ የደም ልገሳ መርሃ-ግብሮችን በማደራጀት
·         የተቸገሩ አረጋውያንን እና እናቶችን መኖሪያ ቤቶች በዘላቂነት በማገዘ
·         ለተቸገሩ ሕፃናት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ግዴታቸውን በተግባር አሳይተዋል።
የቤተሰብ እና የወላጆች ወርሃዊ ፕሮግራም መድረክ (Parenting Program) ትልቁ የህይወት ጥሪሳቸው የተቀሰቀሰው በየዓመቱ በኤልገል ሆቴል በሚካሄደው የልጆች የበጋ ካምፕ ወቅት በህፃናት ላይ የሚታዩ  ክፍተቶችን የወላጆች የአስተዳደግ መዘናጋት ያመጣቸውን ተፅዕኖዎች በቅርበት በመገንዘብ ነበር የስነ-ምግባር እና የማንነት ቀውሶች መንስኤያቸው ከቤተሰብ አያያዝ ጋር የተያያዘ መሆኑን በመረዳት «የኤልገል የወላጆች መድረክ»ን (Elgel Parenting Program) መስርተዋል። በመድረኩም የሚከተሉት ጥልቅ ስልጠናዎች በባለሙያዎች ታግዘው ተሰተዋል፦
1 ከላንሴት ሕክምና ማዕከል ባለሙያዎች ጋር በመሆን የጨቅላ ሕፃናት ጤና አጠባበቅ እና የንግግር መዘግየት ቴራፒዎች ላይ ያተኮሩ ጠንካራ ስልጠናዎችን ተሰጥተዋል።
2 የእናቶችና ታዳጊዎች ቁርኝት፦በቅርብ ጊዜ ከፍተኛ ተወዳጅነትን እያተረፉ ልብ የሚነኩ   ከ13 እስከ 19 ዓመት የሆኑ ታዳጊ ሴት ልጆች ከእናቶቻቸው ጋር በግልጽነት፣ በፍቅር እና በወዳጅነት የተሞላ ግንኙነት እንዲፈጥሩ ማገዝ (Bridging Mothers & Teen Girls)።
3 ወሳኝ አስተሳሰብ እና ራስን ማሳደግ (Critical Thinking & Self-development)
4 የተፈጥሯዊ የቆዳ እንክብካቤ (Herbal Skincare makeup and nutrition ) ግንዛቤ ማስጨበጥ።
5 ስነ-ልቦናዊ የቤተሰብ ድጋፍ ጤናማ ጋብቻ መሰረቶች፣ ፍቺ በልጆች ስነ-ልቦና ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት መቀነስ፣ single mom ጥንካሬ፣ ከማንነት ቀውስ መውጣት
·         ትንኮሳን መቋቋም (Overcoming bullying and its consequences)
·         የእኩዮች ግፊትን መቋቋም (Resistance to peer pressure and its impact)
·         ከሱሰኝነት ማህበራዊ ተጽዕኖ ነፃ በሆነ ማህበረሰብ ውስጥ ልጆችን የማሳደግ ጥበብ
«የአረንጓዴ አሻራ የወላጆች መድረክ»ን በመፍጠር የነገዋን ኢትዮጵያ ቤተሰብ በመገንባት ላይ የሚገኙትን ወ/ሮ ሰናይት በዙ ዛላበረከቱት ታላቅ አስተዋፅኦ የ9ኛው የእንቁ ሴት ንቁ ሴት ሽልማትን ማግኘት ችለዋል።

የሥራ ፈጠራ

የሥራ ፈጣሪዋ በሕይወት መንገድ ላይ የወደቁባቸውን ተፈታታኝ ፈተናዎችን መከራዎችን በሙሉ በጽናት አልፈው፣ዛሬ ላይ በፅኑ እና በሚያስገርም የሰብዕና ጥንካሬዋ የአያሌዎችን ልብ የማረኩ ድንቅ ሴት ለመባል በቅተዋል። ይህ የማይበገር ጥንካሬ የከበረ ስብዕና ግን እንዲሁ በባዶ ቦታ ላይ የበቀለ አይደለም፤ ይልቁንም አስተዳደጋቸውና መነሻቸው በሆነው በዚያ የፍቅር፣ የድጋፍ እና የማያቋርጥ ድካም መገለጫ በነበረው የቤተሰባቸው መለስተኛ የሬስቶራንት ንግድ ውስጥ የተቀረጸና የበሰለ ነው:: በዚያ የጥረትና የትጋት ድባብ ውስጥ ሆነው ከቤተሰብ የቀሰሙት የፅናት፣ የትህትና እና የጥንካሬ ትምህርት ለዛሬው ማንነት ላቅ ላለ ስብዕናዋ ጠንካራ መሠረት እንደሆነላቸው ይናገራሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *