አገራቸውን በልዩ ልዩ መንገድ ፣በተለይም ከዕውቀትና ከዕድገት ጋር በተያያዘ ያገለገሉት የሕይወት ታሪካቸውን ሊያስነብቡ እንደሆነ ታወቀ፡፡
“ከእናት እቅፍ እስከ ልጅ ልጅ ምርኲዝ ትዝታዎቼ ” የሚል ርዕስ የተሰጠው ይህ መፅሐፍ 350 ገፆች አሉት፡፡
ዶክተር ያየህይራድ ቅጣው ከጄነራል ዊንጌት ብርቱ ተማሪዎች አንዱ የነበሩ ሲሆን በፈረንሳይ አገርም የህክምና ትምህርታቸውን ለመከታተል የቻሉ ናቸው፡፡
የዕድገት በሕብረት ዘመቻ ላይ የማይዘነጋ አሻራ ያኖሩት ዶክተር ያየህይራድ ቅጣው፣በትምህርት ሚኒስትርነት እናት አገራቸውን በትጋት ያገለገሉ ናቸው፡፡
የመፅሐፉ ሙሉ ረቂቅ በዶክተር ያየህይራድ ቅጣው የተሰናዳ ሲሆን ከተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን በጋዜጠኛ ዕዝራ እጅጉ አስተባባሪነት ናይእግዚ ኅሩይ የአርትዖት ሥራውን ፈጽመዋል።
የዶክተር ያየህይራድ ባለቤትና ልጆች ፣ለዚህ መፅሐፍ ትልቅ ትብብር ያሳዩ ሲሆን መፅሐፉም ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንደሚመረቅ ታውቋል።