ታሪክን የኋሊት

ይህ ፎቶ 36 አመት ወደ ኋላ ይወስደናል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበባት ተማሪዎች ማለትም የ1981 እና የ1982 ባቾች በምስሉ ላይ ይታያል፡፡ ይህ ምስል በአጋጣሚ ከአንድ ስርቻ ስር የተገኘ ሲሆን ነገር ግን ታሪካዊ ነው፡፡ በምስሉ ላይ ያሉት ሰዎች በሀገራችን የመረጃ እና የመዝናናኛ ስራ ውስጥ የጎላ ድርሻ የነበራቸው ናቸው፡፡ እኔ የማውቃቸውን በደረስኩበት መረጃ ልክ ማን እንደሆኑ ለማስረዳት እሞክራለሁ፡፡
ከኋላ የቆሙት

  1. ካወቁት ይንገሩኝ
  2. ጌታቸው ታረቀኝ ቢጊዮሎጂ ደራሲ፡፡ አሁን ዶክተር ነው፡፡የቴአትርና ባህል አዳራሽ ስራ መሪ ነበር፡፡ በቴአትር ጥበባት ጥሩ ነጥብ አምጥቶ ቀርቶ ያስተምር ነበር፡፡ አሁን በአይሲቲ ዶክትሬቱን ይዞአል፡፡
  3. ግርማ ደገፋ ለረጅም አመት በኢቲቪ ከአድማስ ባሻገርን ሲያዘጋጅ ነበር፡፡ የ1982 ምሩቅ ነው፡፡ 120 በ1984 ሲጀመር ከጀመሩት አንዱ ነው፡፡ ባለቤቱ አቦነሽ መንግስቱ ስትባል በአሁኑ ሰአት በአሜሪካ ይኖራሉ፡፡
  4. ካወቁት ይንገሩኝ
  5. ተፈራ መኮንን በስነጽሁፍ ማስትሬት ያለው መከላከያ ውስጥ ጥሩ ጥሩ የስነጽሁፍ ስራዎችን ያበረከተ፤ በፈርጥ መጽሄት ላይ የሰራ ፤ እንዲሁም በእለታዊ አዲስ ጋዜጣ ላይ ያገለገለ በተጨማሪም ደግሞ መመረቂያ ወረቀቱን በሼክስፒር ስራዎች ላይ የሰራ በአሁኑ ሰአት በፋና በስራ ሃላፊነት የሚሰራ
  6. አላውቅም
  7. ዘላለም ጌታሁን … በፋና ብሮድካስቲንግ በዳይሬክተርነት የሚሰራ
    ከተቀመጡት
    2.1 አላወቅኩም
    2.2 መሰረት አታላይ በኢትዮጵያ ቲቪ እና ሬድዮ የኪነጥበብ አዘጋጅ የነበረ
    2.3. አንተነህ ሀይለማርያም በአሁኑ ሰአት በብረት ቢዝነስ ላይ የተሰማራ ለተወሰኑ ጊዜያት በባህል መምሪያ የሰራ ፤ ከዚያም ወደ ቻይና አቅንቶ በፊልም ማስተርሱን የሰራ ፤ ተማሪ እያለ ቮልስ ይዞ የሚመጣ
    2.4 ማናት
    2.5 ሳህሉ ኪዳኔ …. አንቲገንን ያዘጋጀ ሜጋ የነበረ … በአሁኑ ሰአት ጋና የሚገኝ
    2.6 ዳንኤል አያሌው …. ኢትዮጵያ ሬድዮ የነበረ ….. የኪነጥበባት ክፍል ይሰራ የነበረ …. የሬድዮ ድራማዎች ገምጋሚ አሁን በስዊድን የሚገኝ መዝገበ-አእምሮላይ ታሪኩ የተሰነደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *