የኢትዮጵያ አየር ኃይል የቀድሞ አባላት

የኢትዮጵያ አየር ኃይል የቀድሞ አባላት

የኢትዮጵያ አየር ኃይል የቀድሞ አባላት በዘነበወርቅ ማገገሚያ ለተጎዱ የሰራዊቱ አባላት እርዳታ አደረጉ:: ለወገን ደራሽ ወገን ነው የሚለውን ብሂል ተከትለው የቀድሞ የአየር ሀይል  አባላት  የበኩላቸውን አድርገዋል፡፡ይህ እገዛ እንደአመቺነቱ ወደፊትም የሚቀጥል ይሆናል፡፡ከቀድሞው አየር ኃይልአባላት  በጦርነቱ ለተጎዱ የሰራዊቱ አባላት  ቱታ ፣ የውስጥ ልብሶች እና ” ለአገልግሎታችሁ እናመሰግናለን ” የሚል ፅሁፍ ያለው ሹራብ  ሊበረከት ችሏል፡፡ ለሴት የሰራዊቱ አባላት የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ የተለያዩ መድሃኒቶችን አስረክቧል ። ስጦታውን ያበረከቱት አቶ ብርሀኑ ሞላ ፤  ካፒቴን ሰለሞን መንግስቱ፤ ካፒቴን ክንዴ ዳምጤ፤ ጁቴክ ሳሙኤል ዜና፤ ጁቴክ ንጉሴ አባ ናቸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *