ለኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ አገልግሎት የሚሰጥ «Mela» የተሰኘ የመጀመሪያው ኒዮባንክ (Neobank) እና ዲጂታል የፋይናንስ መድረክ በይፋ ሥራ ጀመረ።
ይህ መድረክ Mela Finance Inc. በተባለ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ ኩባንያ የበለፀገ ሲሆን፣ የኢትዮጵያን ዲያስፖራ የተበታተነ የፋይናንስ ሕይወት በአንድ ማዕከል ሥር ለማገናኘት ያለመ ነው።
በመጀመሪያው ምዕራፍ በአሜሪካ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን፣ የሚያቀርባቸው ዋና ዋና አገልግሎቶችም፦
የአሜሪካ የባንክ ሂሳብ ተደራሽነት እና የቀጥተኛ ደመወዝ ገቢ አገልግሎት ዲጂታል የገንዘብ አስተዳደርና የባንክ ሂሳብ ማገናኘት
በሕጋዊና ፈቃድ ባላቸው መንገዶች ወደ ኢትዮጵያ የባንክ ሂሳቦች ገንዘብ መላክን ያካትታል።
Mela የሂሳብ ወርሃዊ የጥገና ክፍያ እንደሌለውና የደንበኞች ድጋፍ አገልግሎቱ በቀን 24 ሰዓት በእንግሊዝኛ፣ በአማርኛ፣ በኦሮምኛ እና በትግርኛ ቋንቋዎች እንደሚቀርብ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከኦገስት 7 ቀን 2026 ዓ.ም ጀምሮ Mela Finance Inc.ን በይፋ ፈቃድ በተሰጣቸው የገንዘብ ማስተላለፊያ ተቋማት ዝርዝር ውስጥ አካትቶታል።
የMela ዋና ሥራ አስፈጻሚና ተባባሪ መሥራች አኤላፍ ሚደቅሳ እንደገለጹት፣ የመድረኩ ዋና ዓላማ ማህበረሰቡ ያለበትን የተበታተነ የፋይናንስ እንቅስቃሴ በማስቀረትና በደህንነት ላይ የተመሠረተ አሰራር በመዘርጋት የዲያስፖራውን ማህበረሰብ መደገፍ ነው ብለዋል።
ተቋሙ በሁለተኛው ምዕራፍ የወደፊት ዕቅዱ ዲጂታል የእቁብ መሳሪያዎችን፣ የቤት ብድርን እና በማህበረሰቡ መካከል የሚደረጉ የንግድ ክፍያዎችን የሚያመቻቹ አሰራሮችን ለማካተት ማቀዱንም ይፋ አድርጓል።