ታምራት ወደ ሚድያ እንዴት መጣ?

ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን የፎርቹን ጋዜጣ መስራች ስለሆነው ስለ ታምራት ገብረጊዮርጊስ የስራ እና የህይወት ታሪክ ረዘም ያለ ጽሁፍ ከዚህ ቀደም ማውጣታችን ይታወሳል፡፡ ከወጡት ጽሁፎች መካከል የይበቃል ጌታሁን እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ ይበቃል ጌታሁን እና ታምራት ገብረጊዮርጊስ ካዛንቺስ መናኸሪያ አካባቢ አደጉ፡፡ ይበቃል ስለ አብሮ አደጉ ታምራት ሲገልጽ ‹‹…. ታምራት በህብር መፅሄት የስራ ጅማሮውን አደረገ፡ ቀጥሎም በ1985 ዓ.ም ወደ ጦማር ጋዜጣ አቀና፡፡ ገና በታዳጊነቱ ነገሮችን የሚያይበት እይታ የተለየ ነበር ። ለጓደኞቹ ሰላነበባቸው መፃሃፍት እና ስላጋጠሙት ጉዳዮች ሲያስረዳ ልዩ ክህሎት ነበረው፡፡›› በማለት የታምራት የታዳጊነት ህይወት በአንባቢነት የተሞላ እንደነበርም ትዝ ይለዋል፡፡

ታምራት ህብር መጽሄት እና ጦማር ጋዜጣ ላይ ከሰራ በኋላ በ1988 ዓ.ም ሶስት ሆነው የከፈቱትን ኢንተርፕረነር ጋዜጣን እውን አደረጉ፡፡ ጋዜጣው ባለ ስምንት ገፅ እንደነበር እና በውስጡ ዜናዎች፣ አርቲክሎች ፣ የተለያዩ ሁነቶችን የሚያሳይ ጋዜጣ ነበር። ‘’ታምራት ለዚህ ስራ ተሰፍቶ የተሰጠ ነው ለስራው ፍላጎት ያለው ነው እራሱን ፕሮፌሽናል ያደረገ እና ለሚድያ መሪ ነው አስተማሪም ነው ‘’ ይለናል። ይበቃል፡፡ ኢንተርፕረነር ለ 2 አመት እንደቆየ በነገሮች አለመመቸት እንደተቋረጠ እና በወቅቱም ለትንሽ ግዜ የኢትዮጵያ ንግድ ቻምበር ጋዜጣ ላይ ታምራት ሰርቷል፡፡ ታምራት አሜሪካን ሀገር የአጭር ጊዜ ስልጠና መውሰዱ በሙያው ላይ ትልቅ ስራ እንዲሰራ መሰረት አስቀምጦለታል፡፡

ታምራት በ1991 ካፒታል ጋዜጣን ከአቶ ክቡር ገና ጋር በጋራ የጀመረ ሲሆን ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በኃላ ግን ካፒታልን ትቶ ፎርቹንን አንድ ብሎ ጀመረ፡፡ የፎርቹን ጋዜጣ ውልደት ታምራትን ደስ ያሰኘ ነገር ነበር፡፡ ታምራት ቀድሞ አብረውት ይሰሩ የነበሩ ጋዜጠኞች በመያዝ ፎርቹን ጋዜጣን መመስረት ችሏል፡፡ በዚያን ወቅት ፎርቹን ሲመሰረት የነበሩ ባለሙያዎች ይበቃል ጌታሁን፤ ሚኪያስ ወርቁ ፤ መላኩ ደምሴ ፤ ሜሪ ደጀኔ ፣አበበ ታደሰ ይጠቀሱ ነበር፡፡ ይበቃል በፎርቹን ውስጥ በግራፊክስ ዲዛይነርነት እና በምክትል ዋና አዘጋጅነት የስራ መደብ ያገለግል ነበር፡፡ ይበቃል እንደሚለው የስራ ባልደረቦቹ ወደ ፎርቹን መምጣታቸው እና የራሳቸውን ስራ መጀመራቸው ትልቅ ነገር እንደነበር ይገልጣል።

የመጀመሪያዎቹ እትሞች በሚወጡ ሰዓት አልጋ በአልጋ እንዳልነበር የሚናገረው ይበቃል በጥረት እና በብዙ ድካም ወደመልካም መንገድ መምጣታቸውን ይገልጻል ። የመጀመሪያ የሰራተኞች ደሞዝ ከ700 እስከ 1500 ነበር። ታምራት በሙያው ላይ በፊት ከነበረበት የህትመት ስራዎቹ በተለየ ፎርቹን ላይ ጨምሮ መስራቱን ይነግረናል። ይበቃል በአሁኑ ሰዓት በሪፖርተር ጋዜጣ የግራፊክስ ክፍል ሀላፊ በመሆን እየሰራ ነው ።
ታምራት ወደ ሚድያ እንዴት መጣ?

ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን የፎርቹን ጋዜጣ መስራች ስለሆነው ስለ ታምራት ገብረጊዮርጊስ የስራ እና የህይወት ታሪክ ረዘም ያለ ጽሁፍ ከዚህ ቀደም ማውጣታችን ይታወሳል፡፡ ከወጡት ጽሁፎች መካከል የይበቃል ጌታሁን እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ ይበቃል ጌታሁን እና ታምራት ገብረጊዮርጊስ ካዛንቺስ መናኸሪያ አካባቢ አደጉ፡፡ ይበቃል ስለ አብሮ አደጉ ታምራት ሲገልጽ ‹‹…. ታምራት በህብር መፅሄት የስራ ጅማሮውን አደረገ፡ ቀጥሎም በ1985 ዓ.ም ወደ ጦማር ጋዜጣ አቀና፡፡ ገና በታዳጊነቱ ነገሮችን የሚያይበት እይታ የተለየ ነበር ። ለጓደኞቹ ሰላነበባቸው መፃሃፍት እና ስላጋጠሙት ጉዳዮች ሲያስረዳ ልዩ ክህሎት ነበረው፡፡›› በማለት የታምራት የታዳጊነት ህይወት በአንባቢነት የተሞላ እንደነበርም ትዝ ይለዋል፡፡

ታምራት ህብር መጽሄት እና ጦማር ጋዜጣ ላይ ከሰራ በኋላ በ1988 ዓ.ም ሶስት ሆነው የከፈቱትን ኢንተርፕረነር ጋዜጣን እውን አደረጉ፡፡ ጋዜጣው ባለ ስምንት ገፅ እንደነበር እና በውስጡ ዜናዎች፣ አርቲክሎች ፣ የተለያዩ ሁነቶችን የሚያሳይ ጋዜጣ ነበር። ‘’ታምራት ለዚህ ስራ ተሰፍቶ የተሰጠ ነው ለስራው ፍላጎት ያለው ነው እራሱን ፕሮፌሽናል ያደረገ እና ለሚድያ መሪ ነው አስተማሪም ነው ‘’ ይለናል። ይበቃል፡፡ ኢንተርፕረነር ለ 2 አመት እንደቆየ በነገሮች አለመመቸት እንደተቋረጠ እና በወቅቱም ለትንሽ ግዜ የኢትዮጵያ ንግድ ቻምበር ጋዜጣ ላይ ታምራት ሰርቷል፡፡ ታምራት አሜሪካን ሀገር የአጭር ጊዜ ስልጠና መውሰዱ በሙያው ላይ ትልቅ ስራ እንዲሰራ መሰረት አስቀምጦለታል፡፡ ታምራት በ1991 ካፒታል ጋዜጣን ከአቶ ክቡር ገና ጋር በጋራ የጀመረ ሲሆን ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በኃላ ግን ካፒታልን ትቶ ፎርቹንን አንድ ብሎ ጀመረ፡፡

የፎርቹን ጋዜጣ ውልደት ታምራትን ደስ ያሰኘ ነገር ነበር፡፡ ታምራት ቀድሞ አብረውት ይሰሩ የነበሩ ጋዜጠኞች በመያዝ ፎርቹን ጋዜጣን መመስረት ችሏል፡፡ በዚያን ወቅት ፎርቹን ሲመሰረት የነበሩ ባለሙያዎች ይበቃል ጌታሁን፤ ሚኪያስ ወርቁ ፤ መላኩ ደምሴ ፤ ሜሪ ደጀኔ ፣አበበ ታደሰ ይጠቀሱ ነበር፡፡ ይበቃል በፎርቹን ውስጥ በግራፊክስ ዲዛይነርነት እና በምክትል ዋና አዘጋጅነት የስራ መደብ ያገለግል ነበር፡፡ ይበቃል እንደሚለው የስራ ባልደረቦቹ ወደ ፎርቹን መምጣታቸው እና የራሳቸውን ስራ መጀመራቸው ትልቅ ነገር እንደነበር ይገልጣል። የመጀመሪያዎቹ እትሞች በሚወጡ ሰዓት አልጋ በአልጋ እንዳልነበር የሚናገረው ይበቃል በጥረት እና በብዙ ድካም ወደመልካም መንገድ መምጣታቸውን ይገልጻል ። የመጀመሪያ የሰራተኞች ደሞዝ ከ700 እስከ 1500 ነበር። ታምራት በሙያው ላይ በፊት ከነበረበት የህትመት ስራዎቹ በተለየ ፎርቹን ላይ ጨምሮ መስራቱን ይነግረናል።

ይበቃል በአሁኑ ሰዓት በሪፖርተር ጋዜጣ የግራፊክስ ክፍል ሀላፊ በመሆን እየሰራ ነው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *