ሀርመኒ ሆቴል  የተመሰረተበትን 15ኛ ዓመት አከበረ    

በታህሳስ 2001 የተመሠረተው፣ በሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ ተሰማርቶ የሚገኘው ሀርመኒ ሆቴል አገልግሎት መስጠት የጀመረበትን 15ኛ ዓመት ጥር 9 2016ዓ.ም አከበረ።

በድርጅቱ ውስጥ ለረጅም አመታት ያገለገሉ ባልደረቦች ተገቢው ዕውቅና የተሰጣቸው ሲሆን በተመሳሳይ መልኩም ደንበኞች ተመስግነዋል።

የሆቴሉ ማኔጅመንት አባላት ፣ ባለአክሲዮኖች በታደሙበት በዚህ እለት የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሀፍታይ ገብረእግዚአብሄር ንግግር አድርገዋል ።

አቶ ሀፍታይ ገብረእግዚአብሄር እንደተናገሩት ሀርመኒ ባለፉት 15 ዓመታት ለብዙዎች የሥራ ዕድል ከመፍጠሩ ባሻገር ጠንካራ የማኔጅመንት ሥርዓት እንዲኖር በማድረግም አይነተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል ።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ስለሺ መላኩ በበኩላቸው ባሰሙት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ሀርመኒ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ለሀገሪቱ በማስገባት በከፍተኛ ግብር ከፋይነትም የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል ብለዋል።

ሀርመኒ በአሁኑ ሰዐት  ለ226 ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን በተለይም ባለሙያዎችን ውጭ አገር ድረስ ልኮ በማሰልጠን ብቃታቸው እንዲያድግ አድርጓል።

በዕለቱ የሀርመኒን የ 15 ዓመት ጉዞ የሚያሳይ ፣ በተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን የተዘጋጀ ዘጋቢ ፊልም የቀረበ ሲሆን ሆቴሉ ወደፊትም የተጠናከረ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተነግሯል። ሀርመኒ ሆቴል የባለ 4ኮከብ ደረጃ ማግኘቱ አይዘነጋም።

የሁነቱ አዘጋጅ ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን የክብረ በዓሉን ዝግጅት ፕሮፌሽናል በሆነ መልኩ እንዲከናወን በማድረጉ ከሀርመኒ ሰዎች አድናቆት ተቸሮታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *