የውጭ አገር ኢንቨስተሮችን የሚያማክር  ኢትዮጵያዊ ተቋም ዛሬ ቢሮውን ያስመርቃል    

ዘገባ ተወዳጅ የመረጃ ማእከል

በቢዝነስ ማማከር እንዲሁም በሎጂስቲክ ተግባራት ላይ የተሰማራው ዋን ስቶፕ ዛሬ መጋቢት 7 2016 ቢሮውን  ያስመርቃል፡፡

 ከ20 በላይ ለሚሆኑ ኢተዮጵያውያን  የሥራ እድል የፈጠረው ድርጅቱ በተለይ ሀገር ውስጥ መዋእለ ነዋይ ማፍሰስ ለሚሹ የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ብዙ እፎይታ እንዳስገኘ ይነገራል፡፡

የድርጅቱ መስራቾች በወጣትነት የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ሲሆኑ ከዚህ ቀደም ይህንን ተቋም ከመመስረታቸው አስቀድሞ  በተሰማሩበት ሙያ በቂ ልምድና እውቀት ያካበቱ ናቸው፡፡የዋን ስቶፕ መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሚክያስ አበራ ይህ ተቋም ከመመስረቱ በፊት የባህር ማዶ ባለ ሀብቶች አገር ውስጥ ኢንቨስት የሚያደረጉበትን መንገድ የማመቻቸት ስራዎችን ሲሰራ ነበር፡፡ በሂደት ግን አንድ ተቋም መስርቶ በተደራጀ መልክ መስራት እንደሚያዋጣ ስለታመነበት አቶ ሚክያስና ጓደኞቹ ዋን ስቶፕን እውን ለማድረግ ችለዋል፡፡

አንድ በአገር ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ የሚሻ ባለሀብት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የህግ  አሰራር በወጉ ተረድቶ ስራውን ለማከናወን እንዲችል ዋን ስቶፕ ተገቢውን ሙያዊ እገዛ ይሰጣል፡፡ ይህም ሲባል እቃውን በጉምሩክ በኩል ከማስመጣት ጀምሮ ሀገር ውስጥ እስከሚገቡ ድረስ ያለውን ሙሉ ሂደት በመከታተል ድርጅቱ ተግባራትን እንደሚያከናውን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ይናገራሉ፡፡

ከቀረጥ ነጻ የሆኑ እቃዎች፣ ፍራንኮ ቫሉታ ኤልሲ የመሳሰሉ ኢንቨስትመንቱን እውን ለማድረግ የሚያግዙ ስርአቶችን በማወቅና ተገቢ ሰነዶች እንዲሟሉ በማድረግ ዋና ስቶፕ የማማከር ሚናውን በአግባቡ ይወጣል፡፡ 

በአሁኑ ሰአት የውጭ ኢንቨስተሮች ሀገር ውስጥ ገብተው እንዲሰሩ የአማካሪ ድርጅቶች ሚና ትልቅ መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ኢትዮጵያ በውጭ ምንዛሪ የደረጀች እንድትሆንና ባለሀብቱም እንዲመጣ ሀገር ውስጥ ያለው አሰራር በዘመናዊነት እና በቅልጥፍና የታጀበ ሊሆን እንደሚገባ የዋን ስቶፕ የሥራ መሪዎች ያምናሉ፡፡  

ዋን ስቶፕ ከሚያማክራቸው የኢንቨስትመንት ተቋማት መካከል ኤን ኤች ቤይ ፈርኒቸር፣ አቢሲኒያ ግሩፕ ኦፍ ኢንቨስትመንት፣የአሊባባ ግሩፕ የሆነው ዌል ክላውድ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ዋን ስቶፕ ይህን የመተዋወቂያ መሰናዶ በሚያከናውንበት እለተ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የተጋበዙ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *