ደበበ ሰይፉ
እንደሚታወቀው ደበበ ሰይፉ ሚያዝያ 16 1992 በ50 አመቱ ያረፈ ገጣሚ ሀያሲና መምህር ነበር፡፡ አርብ ሚያዝያ 19 2010 ከጠዋቱ 4ሰአት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማእከል በሚደረገው የመታሰቢያ ዝግጅት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ተማሪዎች እንዲሁም ደበበ ሰይፉ ያስተማራቸው ባለሙያዎች ይታደማሉ፡፡
በእለቱ የደበበን ታሪክ የሚተርክ ባለ 22 ደቂቃ ዘጋቢ ፊልም የሚታይ ሲሆን የደበበን የልጅነት ምስል የሚያሳዩ የሰራቸውን የስነ ጽሁፍ ስራዎች የሚያስቃኙ ፎቶግራፎችም ይቀርባሉ፡፡ በዚሁ እለት ደበበ ያስተማራቸው የቀድሞ ተማሪዎች በደበበ የማስተማር ክህሎት ላ ይ ሀሳብ አስተያየት ይሰጣሉ