ማርች 20 በየአመቱ የፈረንሳይኛ ተናጋሪዎች ቀን ወይም ‹‹ፍራንኮፎን ዴይ›› በሚል መርህ ይከበራል፡፡ ካለፈው ማርች 14 -30 ድረስ ይህ በአል አፍሪካን ጨምሮ በመላ አለም ባሉ ሀገራት ይከበራል፡፡
እንደሚታወቀው‹‹ የፈረንሳይኛ ተናጋሪዎች›› ቀን በመላ አለም መከበር የጀመረው በአፍሪካዊትዋ ሀገር በኒጀር ነበር፡፡ በኒጀር ከተማ በኒያሚ ማርች 20 ‹‹የኒያሚ ኮንቬንሽን›› ከተፈረመ በኋላ፣ ላለፉት 48 አመታት የፈረንሳይኛ ተናጋሪዎች ቀን በልዩ ልዩ ክንውኖች ታስቦ ይውላል፡፡ በተናጋሪዎች ብዛት ከአለም 5ኛ የሆነው ፈረንሳይኛ በአለም ላይ 200ሚልዮን ተናጋሪዎች አሉት ፡፡
ይህን ቀን የበለጠ ለማድመቅ ሙዚቃ እንደአንድ መሳሪያ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ሙዚቃ የአለም ቋንቋ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት የአለም ህዝቦችን ለማቀራረብ ቀኑ በደመቀ ሁኔታ ይከበራል፡፡
አሁን የምንመለከታቸው ህዝቦች ከተለያዩ የአለም ክፍል የመጡ ፈረንሳይኛ ተናጋሪዎች ናቸው፡፡ አድሪያና ታነስ የዚህ የሙዚቃ ቡድን መሪ ስትሆን‹‹ ከየትኛውም የአለም ክፍል ብንመጣ ሁላችንም አንድ ጀልባ ላይ እንዳለን አድርጌ እቆጥራለሁ‹‹ ስትል ሀሳብዋን ትሰጣለች፡፡ በሙዚቃ ቡድኑ ውስጥ ያሉ አባላትም ምንም ከተለያዩ ሀገራት ቢመጡ ልዩነት ሳይገድባቸው ጥልቅ የሆነውን የሙዚቃ ፍቅራቸውን ይወጣሉ፡፡
ይህ ቀን በአፍሪካም በስፋት ታስቦ የሚውል ሲሆን በመላ አለም 1500 የሚሆኑ ክንውኖች በዚህ ቀን ይደረጋሉ፡፡ ወደ ድርሰቱ አለም ስንገባ ከሴኔጋል ከማሊ ÷ከአልጄሪያ የተገኙ የኪነ-ጥበብ ሰዎች ባለፉት አመታት ስራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡
የ‹‹ፍራንኮፎን ቀንን›› ምክንያት በማድረግ ከማርች 14 አንስቶ እስከ ማርች 30 ድረስ በመላ አለም የተለያዩ ዝግጅቶች ተደርገዋል፡፡ በሀገራችንም ትናንት ቅዳሜ በአሊያንስ ፍራንሴስ በአሉ በልዩ ልዩ መሰናዶዎች ተከብሮአል፡፡ ትናንት በአሊያንስ ፍራንሴስ ከጠዋቱ 3ሰአት አንስቶ እስከ ማታው 3 ሰአት በርካታ ዝግጅቶች ነበሩ፡፡
ከእነዚህም ውስጥ የጃዝና የሰርከስ ትርኢት የቀረበ መሆኑ ታውቆአል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ፈረንሳይኛ ተናጋሪ የሆኑ የሞሪታንያየሙዚቃ ባንድ አባላትም ለዝግጅቱ ድምቀት የሙዚቃ ስራቸውን አቅርበዋል፡፡ በሀገራችን በተደረገው በዚህ ታላቅ ስነ-ስርአት አምባሳደሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተጋብዘዋል፡