የእኔና ጋሽ አስፋው ትውውቅ

ጋሽ አስፋው

አንድ

ማትሪክ በወሰድኩ በአመቱ፡፡ በ1990 መሆኑ ነው፡፡ 19 አመት ሳይሞላኝ፡፡ ስድስት ኪሎ የ1ኛ አመት ተማሪ ሳለን ፡፡ ከውድ አብሮ አደግ ጉዋደኛዮ ጋር ከናይእግዚ ህሩይ ጋር የልጆች መጽሄት ለመጀመር ከንግድና ኢንዱስትሪ ፍቃድ አወጣን፡፡ከዛም እንግዳ ሊሆኑ የሚችሉ በተለይ ልጅነታቸውን ሊያወሩ የሚችሉ በሚል ጋሽ አስፋውን መረጥን፡፡

በምን አጋጣሚ ማን ስልካቸውን እንደሰጠኝ ባላውቅም ብቻ ተገናኝተን በዛን ወቅት ቃለ-መጠይቅ አደረግኩላቸው፡፡ እንዴት ተባባሪ ሰው እንደሆኑ ይታሰበኛል፡፡

በወቅቱ የ63 አመት ሰው ነበሩ፡፡ ምርጥ ምርጥ ምስል ሰጡኝ፡፡ ለአዲሲትዋ መጽሄት ምን ያህል አሪፍ እንደነበር አስቡት፡፡

እኔም ናይእግዚም ትኩስ የ19 አመት ልጆች ነበርንና ደስታችን አየለ፡፡ ምን ም መጽሄትዋ ለመታተም ባትችል የ2 ወር ባክሎግ ሰርተን ንግድ ፈቃዱ ተመለሰ፡፡ ጋሽ አስፋው ግን ያኔ የሰጡን ሞራል አሁን ድረስ አቆየን፡፡

ሁለት

2010፡፡ ታህሳስ 1 ፡፡ ራስ ሆቴል፡፡ የአክሊሉ ሀብተ-ወልድ ዲቪዲ የተመረቀ እለት፡፡ ጋሽ አስፋው ታድመው ነበር፡፡ አቤት መታደል፡፡ ታድያ ባለፉት 20 አመታት ጋሽ አስፋውን እየወደድኩ ለምን አንድ ነገር አልሰራም እያልኩ አስብ ነበር፡፡ ቀን መጣ፡፡

ሶስት

ደራሲና ሀያሲ አስፋው ዳምጤ ዛሬ መጋቢት 10 የ83ኛ አመት የልደት በአላቸውን ያከብራሉ፡፡ ጋሽ አስፋው የተወለዱት መጋቢት 10 1927 ነበር፡፡ ጋዜጠኛ እዝራ እጅጉ በተወዳጅ ሚድያ አማካይነት ታሪካቸውን በ50 ደቂቃ በኦድዮ ሲዲ ለማሳተም መሰናዶውን አጠናቅቆአል፡፤ ከ20 ቀን በሁዋላ ለገበያ ይቀርባል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *