8ኛ የግለ-ታሪክ የሲዲ አልበማችን አርብ መጋቢት 21 2010 ይወጣል

ድርጅታችን ተወዳጅ ሚድያ በ15 ወራት ውስጥ 8 የግለ-ታሪክ የሲዲ አልበሞችን ማውጣቱን ሲገልጽ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡ አሁን ደግሞ ሀገራችንን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ስላገለገሉት ስለ ልጅ እንዳልካቸው መኮንን የ37 ደቂቃ ዘጋቢ በዲቪዲ ሊያቀርብ ነው፡፡
ከ47 አመት ቀደም ብሎ ሀገራችን ለተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሀፊነት ዕጩ ማቅረቧን ያውቃሉ?

እኚህ ዕጩ በጥቂት ነጥቦች ብቻ 4ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ የመሆን እድላቸውን አጥተዋል፡፡ ሆኖም ብርቱ ተፎካካሪ መሆናቸው ተነግሮላቸዋል፡፡ እኚህ ሰው በወቅቱ የ43 አመት ሰው ነበሩ፡፡ በአቃቂ ሚሲዮንና በቀሀስ የተማሩት የሀገር ልጅ ወደ ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲም ገብተው ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ናቸው፡፡ ሰውየው በ1966 ሀገራችንን ለ4 ወራት በጠቅላይ ሚኒስትርነት አገልግለዋል፡፡ ልጅ እንዳልካቸው መኮንን፡፡ ልጅ እንዳልካቸው መኮንን የአክሊሉ ሀብተወልድ ካቢኔ ከለቀቀ በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉና በህዳር 14 1967 በግፍ ከተገደሉ ከ60ዎቹ የጃንሆይ ባለስልጣናት አንዱ ናቸው፡፡

ተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን ስለ እኒህ ሰው ማለትም ስለ ልጅ እንዳልካቸው መኮንን ባለ 37 ደቂቃ ዘጋቢ ፊልም ሰርቶ በዲቪዲ ሊያቀርብ ነው፡፡ ይህ በዲቪዲ የቀረበ ታሪክ ከዚህ ቀደም ብዙ ያልተደመጡና ለእይታ ያልበቁ የልጅ እንዳልካቸውን ምስልና ንግግር ያካተተ ነው፡፡ የዚህ ዘጋቢ ፊልም ዋና አዘጋጅና አሳታሚ እዝራ እጅጉ ከዚህ ቀደም የጸሀፌ-ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተ-ወልድን ታሪክ እንዲሁም የሌሎች 7 የሀገር ባለውለታዎችን ታሪክ በሲዲ ማሳተሙ ይታወቃል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *