ዳሸን ባንክ 28ኛ አመቱን ነገ ያከብራል

በግል ባንክ ኢንዱስትሪው መስክ ግንባር ቀደም ሚና የተወጣው ዳሸን ባንክ የተመሰረተበትን 28ኛ አመት ነገ በሚሊኒየም አዳራሽ ያከብራል፡፡
ጥር 26 2016 በሚከበረው በዚህ በአል የድርጅቱ ባልደረቦች የሚታደሙ ሲሆን ልዩ ልዩ የመዝናኛ መሰናዶዎችም ይኖራሉ፡፡ በተቋሙ ውስጥ ከ 25 አመት በላይ ያገለገሉ ባለሙያዎች ልዩ እውቅና የሚቸራቸው ይሆናል፡፡
በዚሁ የምስረታ በአል ላይ የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የሚገኙ ሲሆን የባንኩ ፕሬዚዳንትም መልእክት ያስተላልፋሉ፡፡
ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን ሁነቱን በቪድዮ እና በፎቶ ለታሪክ የሚያስቀር ሲሆን የዘጋቢ ፊልም ሥራውንም ለባንኩ ያዘጋጃል፡፡ በዘጋቢ ስራው ላይም ቀደምት የባንኩ የምስረታ ታሪክም ይዳሰሳል ተብሏል፡፡

ዳሸን ባንክ የተቋቋመው በመስከረም 1987 በ14.9 ሚሊዮን ብር ሲሆን መስራቾቹም አሥራ አንድ ባለ ራእይ ባለ አክሲዮኖች ናቸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *