ከዕዝራ እጅጉ
ኢትዮጵያ በአፈሯ ያልተወለዱባት እና ከተወለዱ እኩል ወይም ከዚያ በላይ ከፍ ባለ ደረጃ ለኢትዮጵያ የሚቆረቆሩላት ጥቂት ወዳጆቿ መካከል አንዱ ፕሮፌሰር ዶናልድ ሌቪን ናቸው። ተመራማሪው፣ አስተማሪው፣ ሶሾሎጂስቱ፣ ስፖርተኛው፣ ታሪክ አዋቂው የእነ ግርማሜ ነዋይ ጓደኛ ዶናልድ ሌቪን ስለ ኢትዮጵያ ብዙ ፅፈዋል።
በተለይ Greater Ethiopia (ትልቋ ኢትዮጵያ) እና Wax and Gold (ሰምና ወርቅ) የተሰኙት የብዙ አመታት የምርምር ስራቸው ውጤት የሆኑት መፅሀፎቻቸው በጣም ድንቆቹ ናቸው።
Greater Ethiopia የሚለው መፅሀፋቸው በኢትዮጵያ ጉዳይ ከተፃፉ መፅሀፎች ውስጥ ከምርጦቹ የሚመደብ ነው።
ፕሮፌሰር ዶናልድ ሌቪን ከ25 አመታት በላይ በጅማ፣ በመንዝ፣ በጎጃም እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች ለረጅም ጊዜ በመኖር እና በመዘዋወር ስለ ኢትዮጵያ የተለያዩ ማህበረሰቦች በሰፊው ጥናት አድርገዋል፣ በቺካጎ ዩኒቨርሰቲም መምህር ነበሩ።
በጁን 16 1931የተወለዱት ዶናልድ ሌቪን ፤ ህይወታቸው ያለፈው በኤፕሪል 4 2015 እንደ አውሮፓ ቀመር ነው ። ሌቪን ትውልዳቸው በኒው ካስል ሲሆን በ 1950 የዛሬ 63 አመት የቢኤዲግሪ ፤ በ1954 ደግሞ የኤምኤ ዲግሪያቸውን ፤ በ1957 ደግሞ የፒኤችዲ ዲግሪያቸውን ለመቀበል ችለዋል “።
My excellency friend Donald Levin.
Far from Ezra
Professor Donald Levin is one of the few friends that Ethiopia wasn’t born on her soil and who cares for Ethiopia at a higher level than those born. The researcher, teacher, sociologist, sportsman, historian and his excellency friend Donald Levin has written a lot about Ethiopia.
Especially Greater Ethiopia (Greater Ethiopia) and Wax and Gold (Same and Gold) their books are amazing.
Their book called Greater Ethiopia is one of the best books written on Ethiopian affairs.
Professor Donald Levin has done extensive research on Ethiopian societies for more than 25 years in Jimma, Menz, Gojam and other places. He was a professor at Chicago University.
Donald Levin who was born on June 16 1931, died on April 4 2015 according to European formula. Levin was born in Newcastle 63 years ago in 1950, MA in 1954, and PhD in 1957.