ሰብለወንጌል አለምሰገድ

የልጅ እያሱ የልጅ ልጅ ልጅ

ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን ያልተነገረላቸው በሚል ሀሳብ የ 5,000,000 ኢትዮጵያውያንን የህይወት ታሪክ ለመሰነድ እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ ሁል ጊዜ ታሪክ የተናጋሪ ጀግኖች ብቻ ሳይሆን በዝምታ የተወጡም ጭምር ስለሆነ ሳይናገሩ ፤ ግን የሰሩ ሰዎችን የህይወት ታሪክ በ250 ቃላት ወይም በአንድ ገጽ በማውጣት እኔ ምን ታሪክ አለኝ የሚለውን አጉል ባህል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እናስወግድ ብለን እነሆ ታሪክ ማሰባሰባችን ቀጥሏzል፡፡ የእርስዎ ታሪክ የኢትዮጵያ ታሪክ ነው፡፡ እናም ታሪክዎን ይላኩ የሰራ ሰው ካለም ጠቁሙን፡፡ በአሁኑ ሰአት ይህን ሀሳብ በመደገፍ የህይወት ታሪኳን ያጋራችን የልጅ ኢያሱ የልጅ ልጅ ልጅ የሆነችው ወይዘሮ ሰብለ ወንጌል አለምሰገድ ነች፡፡ የሰብለን ታሪክ እዝራ እጅጉ እና ሀና ምንዳሁን እንደሚከተለው አሰናድተውታል፡፡

ከንጉሳዊ ቤተሰብ የዘር ግንድ ያላቸው የልጅ እያሱ የልጅ ልጅ ልጅ ሰብለወንጌል አለምሰገድ በአዲስ አበባ ጉለሌ በተሰኘው ቦታ ከአባታቸው ልጅ አለምሰገድ አበበ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ያምሮት አስማማዉ በአሁን ስማቸዉ እሙሀይ ያምሮት በ1964 አ.ም ተወለዱ። የአፀደ ህፃናት ትምህርታቸውን በአሳይ ከዛም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በቤተልሄም እና በኒው ኤራ ከተማሩ በኃላ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በመነን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አጠናቀዋል ።

ከዩኒቲ ዩንቨርስቲ ኮሌጅ የህግ ትምህርታቸውን ለሶስት አመታት ተከታትለዋል። በውጪ ሃገራት በመሄድ እ.ኤ.አ በ2007 የውበት ማሳመሪያ ትምህርትንም የተማሩ ናቸው። በ2008 በፈረንጆች በፎቶ ረዳት እንዲሁም በፋሽን አማካሪነት ለ3 አመታት አገልግለዋል። እንዲሁም በ2015 በፈረንጆች WISAG Airport Service Berlin በትኬት ሽያጭ ባለሙያነት እና በ ግራውንድ ሆስተስ በተርሚናል ሰርቪስ ውስጥ ለ ሶስት አመታት አገልግለዋል። እንዲሁም በ2018 እ.ኤ.አ Firma PNA በተባለ የፋሽን ልብስ መሸጫ ውስጥ በመሸጥ እና በአማካሪነት ለ ሁለት አመት ያገለግሉም ናቸው።

በሃገራቸው በኢትዮጵያም እያሉ ከዛሬ ሃያ አምስት አመት ገደማ ሶስት የቴሌቪዥን ማስታወቂያዎችን ሰርተውም ነበር ። እነሱም ጆጆባ አሉቬራ የፀጉር ትርቲመንት፣ አቢሲኒያ ሻይ እና ቡሬ ዉሀን ከአንጋፋው የማስታወቂያ ባለሙያ ከዉብሸት ወርቃለማሁ ጋር ሰርተዋል። በ 2019 እ.ኤ.አ ጀምሮ በተለያዪ የመንግስት ማዘጋጃ ቤት እና በተለያዩ መስሪያ ቤቶች እንዲሁም ኤቬንቶች ላይ እና ፋሽን ዊክ ላይ እየሰሩ ይገኛል።

ወ/ሮ ሰብለወንጌል በማህበራዊ ህይወታቸው በተለያዩ ማህበራት እና ድርጅቶች ላይ በመሳተፍ የሃገራቸውን የኢትዮጵያን ባህል በልጆች ላይ የሚሰራ ማህበር በማቋቋም ተሳትፈዋል። የሃገራቸውን ባህል በስፋትም የቡና አፈላል ባህልን በማስተዋወቅ በሰፊው ሰርተዋል። እንዲሁም ቅድመ አያታቸው ስለሆኑት ስለ ልጅ እያሱ በሰዎች ዘንድ ትክክለኛ ምልከታ እንዲኖር እና እምብዛም ስለማይታወቁባቸው ታሪኮች እና የዲፕሎማሲ ጉዞዋቸው በጥልቀት በማስረዳት ለአሁኑ ትውልድ ታሪክን በማሳወቅ ላይ ይገኛሉ።

የሃገራቸውን ባህል በማሳወቅ በ2012 የባህል አምባሳደር በመባል ከኢትዮጵያ ሽልማት ተቀብለዋል። በ2008 እ.ኤ.አ ኢትዮጵያን ወክለው African Queen In Germany በተሰኘ ውድድር ላይ ተሳትፈው Queen of the Heart በሚል ዘርፍ በሁለተኝነት አሸናፊም ነበሩ።

አሁን ላይ በጀርመን ሃገር በርሊን ከተማ ውስጥ በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ በመስራት ላይ ይገኛሉ። ወ/ሮ ሰብለወንጌል አለምሰገድ የአንድ ልጅ እናት ናቸው።መልካም ዘመን ይሁንላቸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *