ዛሬ መስከረም 1 2015 በፋና ቲቪ አንድ አስተማሪ እና ዘና የሚያደርግ መሰናዶ ተመለከትኩ፡፡ ‹‹የፋና ጋዜጠኞች አስደማሚ የበአል ጨዋታ ››ይሰኛል መሰናዶው እጅግ በጣም ወድጄዋለሁ፡፡ 1 ሰአት ከ14 ደቂቃ ተደምሜ የተመለከትኩት ፕሮግራም ነበር፡፡ የዚህ ፕሮግራም ሀሳብ ፈጣሪዎች እና የእቅዱ ባለቤቶች ምንጊዜም ትችላላችሁ የምላቸው ሳምራዊት ተወልደ እና በእምነት ዘላለም ናቸው፡፡ ሁለቱ ተስፋ የሚጣልባቸው የሚድያ ሰዎች ይህንን 74 ደቂቃ የፈጀ መሰናዶ ለእኛ ለተመልካች እንዲበቃ አስበው ፕሮዲዩስ በማድረጋቸው ልናደንቃቸው ይገባል፡፡
ይህ መሰናዶ 17 የሚጠጉ የፋና ቲቪ መዝናኛ ባልደረቦችን ያሳተፈ ሲሆን 17ቱ በ3 ቡድን ተከፍለው ነበር ተግባራቸውን ሲወጡ የነበረው፡፡ ሰበታ በሚገኘው አንድ የእርሻ ቦታ፤ ናይጄሪያ ኤምባሲ በሚገኘው የእንስራ የሸክላ ስራ እንዲሁም በስለ እናት የበጎ አድራጎት በመገኘት የባለሙያዎቹን የቀን ውሎ አብረው ተካፍለዋል፡፡ ይህን ፕሮግራም በጣም የወደድኩበትን ምክንያት በዝርዝር ላስቀምጥ
- ሲታይ የማዝናናት አቅም አለው፡፡ሁሉም አባላት ንቁ ነበሩ፡፡ ከመግቢያው ጀምሮ ይዞ የማቆየት ልዩ መስህብ አለው፡፡በተለይ በመዝናኛ ስራ በቀጥታ ስርጭት በቂ ልምድ ያካበቱ ጋዜጠኞች ጎልተው ወጥተዋል፡፡
- የማስተማር፤ የማሳየት ግብ ያለው ፕሮግራም ነው፡፡
- 18ተሁኖ በቡድን 74 ደቂቃ የሚፈጅ ፕሮዳክሽን መስራት እንደሚቻል ለሌሎች ያስተማረ ድንቅ ቅንብር ነው፡፡ እንዴት አሳጥሮ ፕሮዲዩስ ማድረግ እንደሚቻልም ያየንበት ድንቅ ቅንብር ነው፡፡
- ጋዜጠኛ ተዝናንቶ ማዝናናት እንደሚችል የታየበት ነው፡፡
- በዳይሬክቲንግ እና በቀረጻም ስናይ የባለሙያዎችን ድንቅ ክህሎት ያየንበት ነው፡፡
- ሴቶች ሀሳብ ከማመንጨት ጀምሮ በስራው ላይ የነበራቸው ተሳትፎ ከ70 ከመቶ በላይ ነው፡፡ የሀሳቡ ባለቤቶችን ጨምሮ 12 ሴቶች በስራው ውስጥ ትልቅ ድርሻ ነበራቸው፡፡
- የመዝናኛ ክፍል ዋና አዘጋጅና ረዳት አዘጋጆችም ያሳዩት ተሳትፎ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡
እንደአጠቃላይ በፕሮግራሙ ላይ የሰዎቹን ውሎ አብረው እየሰሩ እያገለገሉ ፤እያገዙ እየበሉ እየጠጡ ማሳየታቸው ፕሮግራሙን ተወዳጅ አድርጎታል፡፡ እናም ፋና እንዲህ አይነት ፕሮግራሞችን በየጊዜው ያስመልክተን፡፡ ባለሙያዎችም ይበረታቱ እላለሁ፡፡ ብራቮ ፋናዎች ,—– እያበላ …. እያጠጣ …. እየቀጣ ያሳደገን ቤት
እዝራ እጅጉ የተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ