ኢሳያስ አስራት

ኢሳያስ አስራት

ጋዜጠኛ ኢሳያስ አስራት Esayas Aserat በሚድያው አለም ከ16 አመት በላይ ቆይታ ያደረገ ሲሆን የሬድዮ ድራማና እና የመድረክ ስራዎችን በማቅረብ ይታወቃል፡፡ ይብልጡኑ አሻራውን ባኖረበት ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከ1000 በላይ ፕሮግራሞችን አየር በማዋል ይታወቃል፡፡ ጋዜጠኛ ኢሣያስ አስራት በወርሃ ነሀሴ 1971 ዓ.ም በቀድሞው ከፍተኛ 7 ቀበሌ 18 ልዩ ስሙ ሞቢል ሰፈረ ሰላም አካባቢ የሁልጊዜም ጀግናዬ ከሚላት ወ/ሮ አየለች አዘነ እና ከአቶ አሥራት አበራ ተወለደ፡፡እርሱ በተወለደበት ሰፈር በርካታ የስነ-ጥበብ፤የስፓርት እና የጋዜጠኝነት ሙያ በርካቶች ባለ ስም እና ዝና ነበሩ፡፡የኢሣያስን የዛሬ ማንነት ከወጣበት የትውልድ ሥፍራው ወላጆቹ ቤት ሰርተው ወደ መካኒሳ እርሱን እና ሁለት እህቶቹን እንዲሁም ወንድሞቹን ጠቅለው በመግባት በዚያው ኑሯቸውን አደረጉ፡፡ ከታዳጊነት እስከ ወጣትነት……..በትምህርትየመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በቀስተ ደመና ከ1-3 ከዚያም በተስፋ የህዝብ ት/ቤት 4ኛ ክፍልን በመካኒሳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ከ5-8 ተማረ፡፡

በተለይም በመካኒሳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በነበረብት ወቅት ኢሳያስ የደረጃ ተማሪ ነበር ፡፡ጎን ለጎንም በት/ቤቱ የሚኒ ሚዲያ ላይ ተሳትፎው የጎላ ሲሆን ጋዜጠኛ የመሆን መንፈሱ ከዚያ ይንደረደራል ፡፡በማስከተልም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በSOS ከፍተኛ 23 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከ9-12 ተከታትሏል፡፡ በዚያም የሚኒ ሚዲያ የኪነ-ጥብብ እና የግጥም ውድድሮች ት/ቤቱን ወክሎ ተሳትፎ አድርጓል፡፡ ከፍተኛ ትምህርት ኢሳያስ በ1993 ዓ.ም አፍሪካ ቤዛ ኮሌጅ በአካውንቲንግ በዲፕሎማ የተመረቀ ሲሆን በኮሌጅ ቆይታው ከትምህርት ጎን ለጎን የተለያዩ የመድረክ አጫጭር ተውኔቶች በመፃፍ በመተወን በኮሌጅ ይታወቃል ፡፡

ቀጥሎም በ 2000 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቲያትር ጥበብ በ BA ድግሪ ተመርቋል፡፡ ኢሳያስ በጋዜጠኛነት እና በኪነ-ጥበብ

  • በ1994 ዓ.ም የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ባዘጋጀው የግጥም ውድድር 1ኛ በመውጣት የምስክር ወረቀትና ሽልማት አግኝቷል፡፡
  • በ1995 ዓ.ም የእርሱ የፈጠራ ስራው በሆነው “የሄዋን አፅም” የተሰኘ ድርሰቱን በተዋናይነት ጭምር በራስ ቲያትር ቤት ለተመልካች አቅርቧል ፡፡ “ማግስት ፊልም” ላይ በ 1995 በትወና
  • ድምጻዊት አበባ ደሳለኝ በትወና የተሳተፈችበትን ማረፊያ የተሰኘው ፊልም ላይ በትወና እና በደራሲነት በ1997 ዓ.ም ላይ አበርክቶ ነበረው፡፡ እስከ 1998 ዓ.ም ድረስ በአእምሮ ፤ሊንኬጅ እና በተለይም ማስታወሻ በተሰኙ የወቅቱ የፖለቲካና የኪነ-ጥበብ ጋዜጦች ላይ በብዕር ስም እንዲሁም በእራስ ስም በኪነ-ጥበብ አምዶች ላይ በተከታታይ ፅፏል ፡፡
  • “እኔና አንቺ ፊልም ላይ 2005 በትወና “ህያው እውነት” ፊልም ላይ በ 2005 በትወና ተሳትፏል የስራ አለም የኢሳያስ የስራ ጅማሬ በ1996 ዓ.ም በ FM 96.3 ሬድዮ የመዝናኛ ዝግጅት ላይ በወግ እና የሬድዮ ድራማ አቅርቧል፡፡ከዚያም በኢትዮጲያ ሬድዮ በ1998 ዓ.ም በወጣቶች ፕሮግራም ላይ ተከታታይ የሬድዮ ድራማ በመፃፍና በመተወን ቀጠለ ፡፡ከዚያም በፊት ከ 1995-1997 ዓ.ም የክፍያ ሰራተኛ በመሆን በከማሺ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት አገልግሏል ፡፡
  • በማስከተልም በ2001 ዓ.ም ወርሃ ጥቅምት በቀድሞው ሬድዮ ፋና በአሁኑ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከሬድዮ እስከ ቴሌቪዢን ጋዜጠኛነት የሚድያ ክህሎቱን በሚገባ አሳይቷል፡፡ከሬድዮ ፋና እስከ ቴሌቪዢን
  • በሬድዮ በሀገር አቀፍ ስርጭት ከማህበራዊ እስከ ኪነ -ጥበብ ያሉ መሰናዶዎችን መላዋን ኢትዮጲያን በመዞር የጋዜጠኛነት ፈታኝ አመታትን በብቃት ለመሻገር የቻለ ብቁ ጋዜጠኛ ነው፡፡
  • ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት |FBC| የቴሌቪዥን ዝግጅት ሲጀመር
  • በፋና ቀለማት
  • በሬድዮ ትረካዎች
  • በ90 ደቂቃ ዜናዎች
  • በዱር ህይወት የብሔራዊ ፓርኮች ጉብኝት መሰናዶዎች ኢሳያስ ተሳትፎው የላቀ ነበር፡፡
  • የኢሳያስ ቀለም በፋና 70/80 የተሰኘ በ1970ዎቹ እና 80ዎቹ ዓ.ም በካሴት የተቀረፁ ሙዚቃዎችን ከነእነ ታሪካቸው በፋና FM 98.1 ሬድዮ ማቅረብ
  • በፋና ቀለማት የቴሌቪዥን ፕሮግራም ግለ-ታሪኮችን ለምሳሌ፡- የአቀናባሪ ሙላት አስታጥቄ የድምፃዊ ተሾመ ምትኩ እና እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) እና አባይ የተሰኙ መሰናዶችዎችን ሌሎችንም የመዝናኛ ስራዎች አየር ላይ ማዋል ችሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *