ወይዘሮ ምሥጋና 1978-2015
የወ/ሮ ምሥጋና ክፍሌ አጭር የሕይወት ታሪክ
ወ/ሮ ምሥጋና ክፍሌ በሐምሌ ወር 1978 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ካዛንቺስ አካባቢ ከአባታቸው አቶ ክፍሌ ወ/ኢየሱስ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ዘብይደሩ ዱሬሳ ተወለደች፡፡
ለቤተሰቧ አራተኛ ልጅ የሆነችው የያኔዋ ህፃን ምሥጋና የልጅነት እና ታዳጊነት ዕድሜዋን በNazareth School የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በመከታተል አሳልፋለች፡፡ በዚሁ የጨቅላነት ዕድሜዋ በዙሪያዋ ባሉ የትምህርት ቤት ጓደኞቿ ብሎም በአብሮ አደጎቿ እና ቤተሰቧ መካከል በመልካም ሥነ- ምግባር የተመሰከረላትና ‘የልጅ አዋቂ’ ያስባላት በሳል ማንነት ገና ከማለዳው የተላበሰችው መለያዋ ነበር፡፡
በቀለም ትምህርቷ ከፊት ቀዳሚዎቹ ተርታ ትሰለፍ የነበረችው ምሥጋና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ባማረ ውጤት ታጅባ በማጠናቀቅና ወደ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት በመሸጋገር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል የመጀመሪያ ዲግሪዋን፤ እንዲሁም በ public policy የሁለተኛ ዲግሪዋንም ከዚሁ ተቋም አግኝታለች፡፡
በትምህርቱ ዓለም የቀሰመችውንና በከፍተኛ ውጤት በመታጀብ ያጠናቀቀችውን ትምህርት ሀገሯንና ህዝቧን ወደምታገለግልበት ደረጃ መሸጋገር በብዙ ድርጅቶች ተፈላጊ ቢያደርጋትም ስትመርጥ መምረጥ የምታውቅበት በሳሏ ምሥጋና ለማህበረሰቡ ይበልጥ ልትጠቅም የምትችልባቸውን ድርጅቶች በመምረጥ በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ በፍጹም ትጋትና መሰጠት ሀገሯን አገልግላለች፡፡ ከነዚህም ውስጥ Advocates Africa, Christian Fellowship, World Vision Ethiopia, እና Irish Aid ከዋነኞቹ ተርታ የሚሰለፉት ናቸው፡፡
በተሰጣት ኃላፊነት ቀልድ የማታውቀውና ለእውነት በእውነት ማገልገል የህይወት መርኆዋ የሆነው ምሥጉ በሥራ ህይወት ባለፈችባቸው መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ሁሉ ሥራዋን ጠንቅቃ በመሥራት የተመሠገነች፣ ፍትህ ሲጓደልና አባይ ሚዛን ክብደት ደፍቶ ስታይ የማታልፍ፣ የሚያስከፍላትን ዋጋ ሁሉ ከፍላ እውነት ሲገዛ እስክታይ ጸንታ የምትሟገት ብርቱ ሴት ነበረች፡፡
የዕድሜዋን መጨረሻ ዓመታትም በመንግስት መዋቅር ውስጥ በመግባት በኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአፈ-ጉባኤ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመሆን የመሪነት ሚናዋን በበዛ የኃላፊነት ሥሜትና ለሀገሯ ያላትን ሁሉ በመስጠት መርህ ስታገለግል አሳልፋለች፡፡
መልከ መልካሟና ሳቂታዋ፤ ሁሌም ከፊቷ የዋህነትና ቁም ነገረኛነት የማይነጥፍባት ወጣቷ ምሥጋና ከ11 ዓመታት በፊት እጅግ ከምትወደውና የህይወት አጣማሪዋ ከሆነው አቶ ያሬድ አንቶኒዎስ ጋር በትዳር በመጣመር የአምስት ዓመት እና የሦስት ወራት ዕድሜ ያላቸው ሁለት ሴት ልጆች በማፍራት ጣፋጭ የትዳር ጊዜያትን አሳልፈዋል፡፡ ጥምረታቸውም ለብዙዎች አስተማሪ እና መካሪ የነበረ ድንቅ ቤተሰብ ነበር፡፡ ምሥጉ በትዳር ውስጥ እንዴት ክርስቶስን መኖርና አጉልቶ ማሳየት እንደሚቻል በግልጽ ያሳየች ሴት ለመሆኗ ከባለቤቷ ጀምሮ በቅርብ የሚያውቋት ሁሉ ይመሰክሩላታል፡፡
ምሥጋና በመንፈሳዊ ህይወቷ በድካምም ይሁን በብርታት ሁልጊዜ የክርስቶስን ተምሳሌትነት ስትከተል የኖረችና ይሄም በቃልም ሆነ በተግባር፤ በቤትም ሆነ በውጭ ባሉት ዘንድ የተመሰከረላት መታወቂያዋ ነበር፡፡ ሁሌም ክርስቶስን መምሰልንና ወደፍጽምናውም ማደግን የህይወት መርኆዋ አድርጋ ያለማመቻመች የኖረች፣ ሁሌም በሁሉ ቦታ በተቻላት አቅም ሁሉ የጽድቅን ኑሮ ለመኖር የተጋች፣ እህታችን ናት፡፡
ይሄንኑ የግል መሰጠት ወደህብረት በማሳደግም ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ በጸሎትና የቤተሰብ አገልግሎት ክፍሎች ውስጥ በማገልገል በጸጋዋ ብዙዎችን ስትጠቅም ኖራለች፡፡ ከአጥቢያ ቤተ-ክርስቲያን በዘለለም በሌሎች ሀገር አቀፍ አገልግሎቶች (Ministries) ውስጥም በቦርድ አባልነትና በአማካሪነት ወደሮጠችለትና በህይወቷ ወዳከበረችው ጌታዋ እስከተሰበሰበችበት ቀን ድረስ አገግላለች፡፡
በለጋ ዕድሜዋ ብዙ ያልተነገረላትና በዝምታ ውስጥ ሆና ለሀገርና ቤተ-ክርስቲያን ብዙ ስታበረክት ያለፉትን ጥቂት አሥርት አመታት የኖረችው ወ/ሮ ምሥጋና ክፍሌ በተወለደች በ37ኛው ዓመት ዕድሜዋ ወደሚወዳትና ዕድሜዋን ሰጥታ ወደኖረችለት ጌታዋ ለሰውኛው ድንገቴ በሆነ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር አምላክ ከዘመናት በፊት በቀጠረላት ቀን እና ሁኔታ ነሐሴ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ወደዘላለማዊው ቤቷ ተሰብስባ አፈርን ወደ አፈር የመመለስ ሥረዓቱም ዛሬ ነሐሴ 29 ቀን 2015 ዓ.ም ቤተሰቧ፣ ወዳጅ ጓደኞቿ እና ቤተ-ክርስቲያን በተገኙበት በዚህ በጴጥሮስ ወጳውሎስ ማረፊያ ሥፍራ ይፈፀማል ፡፡
እግዚአብሔር አምላክም በመለየቷ ልባቸው ያዘነባቸውን ሁሉ ያጽናና!
እግዚአብሔር ይባርካችሁ
FDRE House of Peoples’ Representatives, the head of the speaker of the office, Mrs. Misegana passed away.
Mrs. Misegana Kifle’s short biography
Mrs. Megana Kifle in July 1978. She was born in Addis Ababa city Kazanchis area to her father Mr. Kifle W/Eyesus and their mother Mrs. Zebyderu Duresa.
The fourth child of her family, Misegana, has spent her childhood and adolescence in Nazareth School attending her primary and secondary education. At this time, her childhood, a mature personality that was witnessed by her school friends around her, her peers and her family.
Megega, who used to be in line with her education in color, has completed her high school education with good results and transferred to higher education, she got her first degree in law from Addis Ababa University, and her second degree in public policy from this institution.
The education that she learned and completed with high results made her needed by many organizations. She has served her country with dedication and dedication in different institutions. Among them Advocates Africa, Christian Fellowship, World Vision Ethiopia, and Irish Aid are among the main ones. They are the ones that line up for a kick.
The one who doesn’t joke about the responsibility given to her and serving the truth honestly was praised for her work carefully in all the offices she spent her life working; she was a strong woman who didn’t pass when justice was lost and when she saw the balance of nobility, she paid all the price she paid and fought until the truth was ruled.
She has spent her last years of her life as the head of the office of the speaker of the house of representatives of FDRE and serving her principles with a sense of responsibility and giving everything she has for her country.
The beautiful and smiling young girl, who is always serious and naive in front of her face, the young Mise, got married 11 years ago with Mr. Yared Antonios, the one she loves and the founder of her life, and had a sweet marriage time by giving birth to two daughters aged five years and three months. Their union was a wonderful family that has been a teacher and mentor to many.
Everyone who knows her starting from her husband will testify that she is a woman who clearly showed how to live and show Christ in marriage.
Grace has always followed the image of Christ in her spiritual life whether in strength or in weakness, this was her identity card that was witnessed by people at home and abroad. She has always made likeness of Christ and growing to perfection her life and has never been comfortable, she has always tried to live a righteous life everywhere.
By growing this personal dedication to fellowship, she has been helping many by her grace by serving in prayer and family service rooms at church. She has recovered from the local church to other national services (ministries) as a board member and counselor to the day she ran to him and was glorified in her life.
Mrs. Misegana Kifle, who was not told much in her early age and has been giving a lot to the church and country for the past few decades, would have been born on 37th year of age to the Lord who loves her and gave her life for her, but on the date and situation God has set for her years ago August 27th 2015 E.C. The ceremony of returning soil to soil is today August 29th 2015 It will be held at Petros Tewulos resting place in the presence of her family, friends and the church.
May God comfort all those whose hearts are grieved by her departure!
May God bless you all