1000 ኢትዮጵያውያን የአማርኛው ዊኪፒዲያ ላይ ታሪካቸው ሊሰፍር ነው

ከ1990 ጀምሮ በኪነ-ጥበብ አንድ ስራ ለሀገር ያበረከቱ ኢትዮጵያውያን አጭር ታሪካችሁ ተጽፎ ዊኪፒዲያ ላይ ይወጣል፡፡
ከ500ቃላት እስከ 1000 ቃላት ታሪክ ካለዎ ተይበው ይላኩልን፡፡ ተባብረን ታሪካችንን እንሰንድ፡፡

በባህር ማዶ ፤ በክፍለ ሀገር ያላችሁ የተቀመጡ መስፈርቶችን የምታሟሉ በtewedajemedia@gmail.com ታሪካችሁን ላኩልን፡፡ ዊኪፒዲያ በሳምንት የ150 ኢትዮጵያውያን ታሪክ እየተቀበለ ስለሆነ ነገ ዛይሉ ዛሬ የተተየበ ታሪክዎን ይልኩልን፡፡ በቀን የ5 ሰዎች ታሪክ እየደረሰን ስለሆነ እርስዎም ይበርቱና ይላኩልን፡፡

በሚድያ ፤ በቴአትር ፤ በሬድዮ ድራማ በማስታወቂያ እንዲሁም በፊልም ዘርፍ ያላችሁ ዘመነኞች እስቲ እንያችሁ ፡፡ እኔ ምን ሰርቼ ታሪኬ ይወጣል የሚል ንግግር ዛሬ አበቃለት፤ ያሁን ወጣት የነገ አዛውንት ነዎትና ታሪክዎን ይሰንዱ ዛሬ ታሪካችን ካልተሰነደ ቀጣዩ ትውልድ ሊያውቀን አይችልም፤ ታሪክዎን በመሰነድ ትብብር ያሳዩ

በዊኪፒዲያ ላይ ታሪካቸው ለሚሰሩ ሰዎች የተዘጋጀ መስፈርት

  1. በሙያቸው ያለማቋረጥ በጽናት ያገለገሉና ለሙያቸው ታላቅ ፍቅር ያላቸው 15 ነጥብ
  2. ከተመደቡበት ወይም ከተቀጠሩበት ስራ አክለው ተጨማሪ ጥረት ያሳዩ 10 ነጥብ
  3. በሙያቸው አዲስ ፈጠራ ወይም በተፈጠረ ጉዳይ ወይም ሀሳብ ውስጥ አንድ እሴት የጨመሩ 10 ነጥብ
  1. በሀገር ፍቅር ስሜት የሚሰሩ( ለሀገራቸው ያላቸው ፍቅር ለሀገር እንዲያስቡ እና ለሀገራቸው እንዲሰሩ ፣ከራሳቸው ይልቅ ሀገራቸውን የሚያስቀድሙ) መሆን ይገባቸዋል 15
  2. በብዙ ፈተናዎች አልፈው አንድ ስኬት ላይ የደረሱና ይህም ስኬታቸው እንዲነገር የፈቀዱ 10
  3. በየጊዜው ለመታየት ሳይሆን በስራቸው ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ የሚታትሩ 10
  4. የስራ ብዛትና ጥራት አመጣጥነው ማስኬድ የሚችሉ 10
  5. በበጎ ፍቃድ የሚሳተፉ -የበጎ ፍቃድ ስራዎችን ያሳኩ 5
  6. የትምህርት ዝግጅታቸውን በየጊዜው ለማሻሻል ጥረት የሚያደርጉ 5
  7. ለለውጥ የሚሰሩ (በስራቸው ገንዘብን መሰረት አድርገው ሳይሆን ለውጥን ለማምጣት በመሻት የሚሰሩ) 5 ነጥብ
  8. በማህበረሰብ ዘንድ የተመሰገኑ እና ጥሩ ስነ-ምግባር ያላቸው 5 ነጥብ

ተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን/ እዝራ እጅጉ /

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *