ፍረወይኒ ገብረህይወት መለስ

ፍረወይኒ ገብረህይወት መለስ

በትግርኛ መጽሀፎችን ደርሳ ለንባብ ያበቃች

የዚህ ታሪክ አሰባሳቢ፣ ተወዳጅ ሚድያና ኮሚኒኬሽን በስነ-ጽሁፍ፣ በስነ-ስእል፣ በፊልም ፣ በቴአትር፣ በሬድዮ ድራማ ፤ በማስታወቂያ ዘርፍ ፤ በሚድያ ዘርፍ ከ1990ዎቹ ጀምሮ አስተዋጽኦ ያበረከቱና አሁንም በስራ ላይ ያሉ ባለሙያዎችን ታሪክ በፌስ ቡክ ፤ በዊኪፒዲያ እንዲሁም በሌሎች የማህበራዊ ሚድያዎች እያስተዋወቀ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ውድ ይህን ሀሳብ የምትደግፉ መስፈርቱን ያሟላሉ የምትሏቸውን ሰዎች ጠቁሙን ፤ ከተቀመጠው መስፈርት አንጻር አይተን ታሪካቸዎን እናወጣለን፡፡

በ tewedajemedia@gmail.com ጥቆማዎን ይላኩ፡፡ ጥቅምት 14 2014 የ1000 ሰዎች ታሪክ ሲሞላ ድንቅ ታሪካዊ ምረቃ ይኖራል፡፡ ታሪካቸው አሁን የሚሰራላቸው፤ ብዙዎቹ በወጣትነት አንዳንዶቹም በጉልምስና እድሜ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ የዛሬ ጎልማሳ የነገ የሀገር ባለውለታ ነውና ታሪካቸውን እየሰነድን ለትውልድ እናስቀምጣለን፡፡ ለወደፊቱም ምርምር ለሚያደርጉ እና ወይም የስራ ፕሮጀክቶቻቸውን ለሚደግፉ ሰዎች ይጠቅማል ብለን እናምናለን፡፡ በ7 ዘርፎች ትልቅ ስራ ሰርተዋል ብለን ያመንባቸውን ሰዎች ታሪክ እናቀርባለን፡፡ ይህ የማስተዋወቅ ስራ ውድድር ሳይሆን በሙያው የተለየ ሚና ያበረከተ ማንኛውም ሰው ታሪኩ የሚሰነድበት ነው፡፡ ጋን በጠጠር ይደገፋል እንዲሉ ሙያቸውን በመደገፍ የራሳቸውን አሻራ ያኖሩ ሰዎች ታሪካቸው ይዘከራል፡፡

በትግርኛ ድርሰቶች መጽሀፍ አሳትመው ለንባብ ካበቁት መካከል  ፍረወይኒ ገብረህይወት መለስ ትነሳለች፡፡ ፍሬወይኒ በዚህ ሙያ 30 አመት የቆየች ስትሆን ታሪኳም እንደሚከተለው  ይቀርባል፡፡

ውልደትና እድገት

በትግራይ ክልል በአዲግራትና በውቅሮ በአስራሁለት ወንድማማችና እህታሞች መሃል ነው ያደገችው፡፡ ከእርሷ በፊት  የተወለዱት ወንድሞቿ በትምህርታቸው ጎበዞች ሰለነበሩ የነሱ ፈለግ መከተል፤ ጎበዝ ተማሪ መሆን ትፈልግ ነበር፡፡ኣባታቸው ዳኛ/የህግ ባለሞያ/ነበርና ፍሬወይኒ  በስድሰት አመቷ ተማሪ ቤት ገባች ፡፡ ‹‹የአባታችን ሙያ ወንድሞቼም በትምህርታቸው የህግ ፍላጎት እንዲኖራቸው ተፅእኖ ፈጥሮአል፡፡›› ትላለች ፍሬወይኒ፡፡ 

እንደጣረችውና እንደፈለገችው  ወደ ከፍተኛ ትምህርት እሚያስገባ ነጥብ ስላልመጣላት፤ ኣስመራ መምህራን ማሰልጠኛ ገብታ የመምህርነት ሞያ የስራ ጉዞ ኣሃዱ ኣለች፡፡

የመምህርነት ቆይታ

ለአስር አመታት በተለያዩ ኣካባቢዎች በመምህርነት ስታገለግል በፍቅር ነበር የሰራችው፡፡የስነ-ፅሁፍና የጋዜጠኝነት ተሰጥኦዋን ያየችበትና  የተለማመደችበትም ነበር፡፡ አጫጭር ግጥሞች መጻፍ፤በስነፅሁፍ ውድድሮች መሳተፍ፤በምታስተምርበት ት/ቤት የስነፅሁፍ ክበቦች መሳተፍና የትምህርትቤት መፅሄቶችን በዋና ኣዘጋጅነት መስራት ቀጠለችበት፡፡ በተለይ በእንዳተካ ተስፋይ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት   “ቆላሕታ”፤በፍረወይኒ 1ኛና መለስተ  ት/ቤት “መስትያት” እሚባሉ መፅሄቶት ከፍተኛ ገበያና ተነባቢነት ነበራቸው፡ ፡

ከመምህርነት ወደ ጋዜጠኝነት

በ1983ዓ/ም ከኤርትራ ወደ ትግራይ ከተመለሰች በኋላ  በተለያዩ የስነፅሁፍ ውድድሮች ትሳተፍና ታሸንፍ ስለነበር በተደጋጋሚ በሚድያ የመቅረብ እድሉ ነበራት፡፡ የተለያዩ ፅሁፎችንም ለሬዲዮ በመላክ ትሳተፍ ነበር፡፡ በ1990ዓ/ም ድምፂ ወያነ ሬድዮ ተወዳድራ እንድትቀጠር በተደረገላት ጥሪ መሰረት  ከተማ ገብታ ከልጅነቷ ስትመኘው የነበረውን ትምህርት መቀጠል ትፈልግ ስለነበር የሬዲዮ ጀማሪ ጋዜጠኛ ሁና ስራ ጀመረች፡፡

በ1996ዓ/ም ክልሎች የራሳቸው የመገናኛ ቡዙሃን እያቛቛሙ ስለነበር በትግራይ የትግራይ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ የቴሌቪዝን ፕሮግራም አንድ ተብሎ ሲጀመር  ከጀመሩት ጥቂት ባለሙያዎች አንዷ ነበረች፡፡ ከጀማሪ ሪፖርተር እስከ ዋና ኣዘጋጅና የመልካም ኣስተዳደርና ምርመራዊ ፕሮግራሞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሁና ሰርታለች፡፡

የትምህርት ዝግጅት

መቐለ የሬድዮ ጋዜጠኝነት ስራን እንደጀመረች ወዲያው በመቐለ ዩኒቨርስቲ በ ቋንቋ የትምህርት ዘርፍ በ1996 ዓ/ም በዲፕሎማ ፤ቀጥላ የመጀመርያ ዲግሪ በ2002ዓ/ም ከሸባ ዩኒቨርሰቲ ኮሌጅ ፤ከዛም የሁለተኛ ዲግሪ በ2009ዓ/ም በውጭ ቓንቓዎችና ስነፅሁፍ ኣጠናቀቀች፡፡

የስነፅሁፍ ጉልበቷ ምንጮችና የስነ ፅሁፍ ጅማሬ

ፍሪወይኒ  የስነ-ጽሁፍ ጉልበቷ  ምን እንደሆነ ስታብራራ እንዲህ ትላለች፡፡

‹‹…..ከልጅነቴ /ተማሪ እያለሁ /በተለይ የቋንቋ  ኣስተማሪዎቼ ይወዱኝ ነበር፡፡ ግጥምና መጣጥፍ ፅፌ በተማሪዎች ፊት ሳነብና ሲጨበጨብልኝ ፍላጎቱና ድፍረቱ ይጨምርልኝ ነበር፡፡ ከዚያም በስነ-ፅሁፍ ውድድሮች መሳተፍ ጀመርኩኝ፡፡ከተወዳደርኩባቸውና ተሸልሜ ከኮራሁባቸው ለምሳሌ፡-

  • በ1980 ዓ/ም በኤርትራ የትምህርት ኣስፈላጊነት ከመሰረተ- ትምህርት ዘመቻ ጋር ተያይዞ በተደረገ ውድድር፡፡
  • በ1989ዓ/ም በትግራይ የመምህርነት ሞያ ኣስመልክቶ በመምህራን ማህበር የተደረገ ውድድር፡፡
  • በ1991ዓ/ም በትግራይ የቤተሰብ ምጣኔ ኣስመልክቶ የተደረገ ውድድር ተጠቃሾች  ናቸው፡፡

የመፃህፍት ኣለም ቤተሰብነት

  • በ2000ዓ/ም “ ጓል መንገዲ” የተሰኘው የግጥሞች ስብስብ መፅሃፍ ከጋደኛየ ጋር በመሆን ፡፡
  • “ኣለሻ” የግጥሞች ስብስብ በ2003ዓ/ም
  • “ሰገን” የህፃናት መፅሃፍ በ2004ዓ/ም
  • “ 3 ቆናጁ ” የኣጫጭር ልብወለዶች ስብስብ
  • “ፍዮሪ” የህፃናት መፅሃፍ በ2007ዓ/ም
  • “ልሳን “የህፃናት መፅሃፍ በ2009ዓ/ም ታትመው በኣንባብያን እጅ ናቸው፡፡

የኪነጥበብ ሽልማቶች የበለጠ ጉልበት ይሰጣሉ

  • “3 ቆናጁ “የትግራይ መንግስት ከትግራይ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ማህበር ጋር በመሆን ባዘጋጀው የውድድር መድረክ በማሸነፍ የማሳተሚያ ሙሉ ወጪ ተሽፍኖላታል፡፡
  • “ሰገን” የህፃናት መፅሃፍ የትግራይ መንግስት ከትግራይ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ማህበር ጋር በመሆን ባዘጋጀው የውድድር መድረክ አሸናፊ ሆነ፡፡                         

ጥናት/ research /

  • በ1988ዓ/ም “ሴቶች ትምህርት የሚያቋርጡበት ምክንያት“ የሴት መምህራን ሚና የሚል በ3 ወረዳዎች የተጠና ያልታተመ ፅሁፍ፡፡
  • 2009ዓ/ም “ክብርታት ኣሸንዳ“ /social values of ashenda songs/ ለሁለተኛ ዲግሪ መመረቅያ፡፡

ህብረተሰብ በነፃ ማገልገል      

  • ከ1986-1987 ዓ/ም በሳዕስዕ ፃዕዳ እንባ ወረዳ የሴት መምህራን ማህበር ሊቀ መንበር
  • ከ 1996-2003 ዓ/ም የትግራይ ሴት ጋዜጠኞች ማህበር ሊቀመንበር፡፡                 
  • ከ 1997-2003 ዓ/ም የትግራይ የኪነጥበብ ባለሞያዎች ማህበር ፀሃፊ፡፡
  • ካብ 1997-2002 ዓ/ም የመቐለ ከተማ ምክርቤት ኣባል፡፡
  • በተጨማሪ የሙዚቃ ኮንሰርቶች፤የገቢ ማሰባሰብያ መድረኮች፤የቴሌቪዝን ቀጥታ ስርጭቶች ወዘተ በመምራትም ላለፍት 20 አመታት ሰርቻለሁ፡፡

የቤተሰብ ሁኔታ

ሁለት ልጆችና ሁለት የልጅ ልጆች ያለው የደስተኛ ቤተሰብ ባለቤት ናት፡፡

ታትመው ለኣንባብያን የተበረከቱ መፅሃፎች

  1. ‘’ጓል መንገዲ ’’መድብል ግጥምታት/ከጋደኛየ ጋር ሁለታችን ያሳተምነው የኣጫጭር ግጥሞች ሰብስብ/                         
  1. “3 ቆናጁ” -መድብል ሓፀርቲ ልብወለዳት /የኣጫጭር ልብወለድ ታሪኮች ሰብስብ/ 
  1. “ኣለሻ ” መድብል ግጥምታት /የግጥሞች ስብሰብ/
  1. “ሰገን” መፅሓፍ ንህፃውንቲ /የህፃናት መፅሃፍ/
  1. “ፍዮሪ ”መፅሓፍ ንህፃውንቲ /የህፃናት መፅሃፍ/
  1. “ልሳን ”መፅሓፍ ንህፃውንቲ /የህፃናት መፅሃፍ/

ማጠቃለያ

ፍሬወይኒ ላለፉት 30 ኣመታት መምህር፣ጋዜጠኛ፣ደራሲና ገጣሚ እንዲሁም መድረክ መሪ ሁና ባሳለፈችው ህይወት ሰኬታማ ነኝ ብላ ታምናለች፡፡ከአንደኛው ሙ ያ የተገኘ ልምድ ለሌላኛው ምርኩዝ እየሆነ፤ በተለይ በጋዜጠኝነት የምርመራ ስራዎች፤የመልካም ኣስተዳደርና የተለያዩ ዶክመንታሪዎች ስትሰራ ፤ ባጠቃላይ በሁሉም  ስራዎቿ  አብረዋት የነበሩ ባለሙያዎች በእጅጉ ማመስገን ትፈልጋለች፡፡ በተለይ የምትወደውን የስነ-ጽሁፍ እና የሚድያ ስራ  አጠናክራ እንድትቀጥል የረዱ ሁሉ ሊመሰገኑ  ይገባል ትላለች፡፡

ስለ ትግርኛ ስነ-ጽሁፍ እና የሚድያ ስራ ስናስብ ፍሪወይኒን በቀዳሚነት ከምናነሳቸው አንዷ ናት፡፡ ፍሬወይኒ ለትግርኛ ስነ-ጽሁፍ ማደግ የበኩሏን ትልቅ አሻራ አኑራለች፡፡ ትናንት ብእር ከወረቀት አዋህዳ የጀመረችው ስራ ዛሬ ታላቅ ክብር እንድትጎናጸፍ አስችሏታል፡፡ ዛሬም ከምርምር ከጽሁፍ ያልተለየችው ፍሬወይኒ ወደፊት ለሀገሯ ትልቅ ነገር የመስራት ራእይ ሰንቃለች፡፡   ይህን የፍሬወይኒን የዊኪፒዲያ ታሪክ የሰሩ ባለሙያዎች እንደሚያምኑት  ይህች ታላቅ ባለውለታ ብዙ ያልተባለላት ስለሆነ ታሪኳን ህዝብ ወይም ትውልድ ሊያውቀው ይገባል በሚል እነሆ ታሪኳን አስፍረናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *