የሀርቫርድ ምሩቁ የቀድሞ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ልጅ የወንድወሰን መንገሻ በ97 ዓመታቸው አረፉ
ዕዝራ እጅጉ-(ተወዳጅ ሚድያ)
ታሕሣስ 24 ቀን 1920 ዓም – ጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ.ም
ቀብራቸው ሐሙስ ጥቅምት 13 በለንደን ይፈፀማል
ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ፣ መዝገበ-አእምሮ ( የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ) ፕሮጀክቱ ለአገር የሠሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ታሪክ በዲጂታል ሚድያዎች ፣በመፅሀፍ፣በድምፅ ትረካና በሌሎችም መንገዶች እየቀረበ እንደሆነ ይታወቃል። ባለፉት 4 ዓመት ከ 5 ወር ጊዜ ውስጥ የ423 ሰዎችን የሕይወትና የሥራ ታሪክ ለመሰነድ የቻልን ሲሆን 600 ገፅ ባላቸው ሁለት የተለያዩ መፅሐፎች ላይም ታሪኮቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድርገናል።
ቅፅ 3 መዝገበ አእምሮ ከ20 በላይ ዘርፎች ይኖሩታል። እዚህ ዘርፍ ውስጥ የሚገኙ የአገር ባለውለታዎችን መሰነዳችን ይቀጥላል። የባንክ፣ የፋይናንስ እና የኢንሹራንስ በሚለው ዘርፍ ውስጥ ታሪካቸው የሚሰነደው ልጅ የወንድወሰን መንገሻ ሲሆኑ ታሪካቸውንም ዕዝራ እጅጉ ሰንዶታል።
የሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የግራጅዌት ቢዝነስ ትምህርት ቤት የታላቅ አገልግሎት እና ለቀድሞ ተማሪዎች የሥራ ስኬት ተብሎ የተሰየመውን ሽልማት ለልጅ የወንድወሰን መንገሻ እ ኤ አ በ1996 ዓ.ም ሲሰጣቸው በመጀመሪያ የእርሳቸውን ማንነት መገለጫ ያደረገው “ሰብዓዊነትን የረዱ” በማለት እና በምስጋናው መዝጊያ ላይ ደግሞ “ለዓለም ደህንነት የታቻላቸውን አስተዋጽኦ ያበረከቱ” ሲል ዩኒቨርሲቲው አድናቆቱን በሚገባ ገልጿል።
የተከበሩ አባታቸው አባ መንገሻ ገነሜ (ቀደም ሲል ፊታውራሪ) የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመድ ነበሩ። እናታቸው ወይዘሮ ተዋበች ዛማኑኤል በወራሪው ፋሽስት በግፍ ታስረው በተወሰዱበት ኢጣልያ አገር ውስጥ ሕይወታቸው አልፏል። አክስታቸው ወ/ሮ ሉልአደይ ዛማኑኤል ልጅ የወንደሰንን እና ታናሽ እህቶቻቸውን ወ/ሪት ኮከቤ መንገሻን እና ወ/ሮ እግዚሐርያ መንገሻን እንደ ልጆቻቸው በፍቅር አሳድገዋቸዋል። ልጅ ከበደ ኃይሌ ታላቅ ወንድማቸው ነበሩ።
ልጅ የወንድወሰን የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በተፈሪ መኮንን እና በፕሪንቺፔ ዲ ፒያሞንቴ ትምህርት ቤቶች ከተማሩ በኋላ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አቃቂ በሚገኘው የአድቬንቲስት ሚሲዮን እና አዲስ አበባ በሚገኘው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተምረው አጠናቅቀዋል። ቀጥሎም፣ በጊዜው የሎንዶን ዩኒቨርሲቲ አካል የነበረው ሳውዝሃምፕተን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተቀብሏቸው በኢትዮጵያ መንግሥት የነፃ ትምህርት ዕድል ድጋፍ ተምረው እ ኤ አ በ1954 ዓ.ም በኢኮኖሚክስ እና አካውንቲንግ በከፍተኛ ማዕረግ ተመረቁ። ኮሌጅ የተማረ የመጀመሪያው የቤተሰቡ አባል እንደመሆናቸው መጠን ወደ እናት አገራቸው ሲመለሱ ሌሎችን ለመርዳት ይጓጉ ነበር። እውቀታቸውን እና ተሞክሯቸውን ለማስፋት ወደ አሜሪካ ሲጓዙ አስፈላጊው ገንዘብ ስላልነበራቸው ቦስተን ለመድረስ ወደካናዳ በሚጓዝ አንስተኛ የውቅያኖስ መስመር ላይ በአስተናጋጅነት በመሥራት ሀሳባቸውን አሳክተዋል። ከእዚያም እ ኤ አ በ1956 ዓ.ም ከሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በኤም ቢ ኤ (MBA) ዲግሪ ተመረቁ።
ልጅ የወንድወሰን መንገሻ ፣ወደ ኢትዮጵያ ከመመለሳቸው በፊት ዶክተር አልበርት ሸቫይጸርን ለማግኘት ምዕራብ መካከለኛው አፍሪቃ ውስጥ ሩቅ ሥፍራ ወደሚገኝ ሆስፒታል ተጓዙ። ሆስፒታሉ ውስጥ ሁለት ሳምንታት ከቆዩ በኋላ ዶክተር ሸቫይጸርን የመሰለ ሌሎችን ለመርዳት የወሰኑ ሰውን መተዋወቅ ለወጣቱ ምሩቅ ታላቅ ክብር ነበር። በሆስፒታሉ ያጋጠማቸው ተሞክሮ በአገራቸው ሕዝብ ሕይወት ላይ ለውጥ ለማምጣት እራሳቸውም በቁርጠኝነት እንዲሰለፉ አድርጓቸዋል።
ወደ የሚወዷት አገራቸው ከተመለሱ በኋላ የመጀመሪያ ሥራ ምድባቸው በኢትዮጵያ አየር መንገድ የከፍተኛ ማኔጅመንት ኃላፊነት ነበር። ቀጥሎም በገንዘብ ሚንስቴር የዳይሬክተርነት ሹመት አገኙ። በዚሁ ሥራቸው ላይ እንዳሉም በወቅቱ በልዑል ራሥ መንገሻ ሥዩም በሚመራው የኢትዮዽያ የአየር መንገድ ቦርድ አባል በመሆን አየር መንገዱ በተለይ አፍሪቃ ውስጥ በተሳካ ሁኔታ የተለያዩ የብሪያ መስመሮችን እንዲዘረጋ የአባልነታቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዎል። የመጀመሪያዎቹን ቦይንግ ጄት ኤሮፕላኖች ለመግዛት በተደረገው ወሳኝ ድርድር ውስጥ ቁልፍ ሚና ነበራቸው።
በ1960 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ሆነው ተሾሙ። ይህንን የተከበረ ቦታ ለመያዝ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ነበሩ። የባንኩን ተቋም ለማዘመን ጠቃሚ ተነሳሽነቶችን በመምራት እና በማስተባበር ለአሥራ አራት ዓመታት በዚያ ሥራ ላይ ቆይተዋል። ከብዙ ትሩፋቶቻቸው አንዱ የብሔራዊ ባንክ ሠራተኞችን ለተጨማሪ ሥልጠና ወደ ውጭ አገር ለመላክ ያደረጉት ብርቱ ጥረት እና ስኬታማ ተነሳሽነት ነበር። ይህ በአርቆ አሳቢነት ላይ የተመሠረተ ጥረት ቁጥራቸው እየጨመረ ለመጣው ልዩ የባንክ ሥራ መደቦች በሙያው የሠለጠኑ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያትን መመደብ አስችሏል።
ልጅ የወንድወሰን መንገሻ የኢትዮጵያ መንግሥትን ወክለው ከሌሎች ሀገሮች የገንዘብ ሚኒስትሮች ጋር በመተባበር በዓለም አቀፍ የባንክ ማኅበረሰብ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ አድርገዋል። በተለይም ልጅ የወንድወሰን መንገሻ የአፍሪቃን ኤኮኖሚ ለማሳደግ እና ድህነትን ለመቀነስ የታለመውን የአፍሪቃ ልማት ባንክን (AfDB) በሚመሠረትበት ጊዜ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል። ኢትዮጵያ መሥራች ባለአክሲዮን እንደመሆኗ መጠን ባንኩን በማቋቋም ረገድ ግንባር ቀደም እና ስኬታማ መሪነት አሳይታለች። ብዙዎች ይህንን ስኬት የብሔራዊ ባንክ ገዥ የአቶ ምናሴ ለማ እና ምክትል ገዥ የልጅ የወንድወሰን መንገሻ አርቆ አስተዋይነት እና አመራር ውጤት ነው ብለው ይመለከቱታል። በዓለም አቀፍ ፋይናንስ ላይ በነበራቸው ዕውቀት እና ባለራዕይ አመራር በ1980 ዎቹ ዓመታት አፍሪቃ ልማት ባንክ ካፒታሉን ለማሳደግ ክልላዊ ያልሆኑ ሀገራትም
(non-regional countries) እንዲሳተፉ መንገድ ከፍተዋል። ይህም ዛሬ የባንኩ የስኬት ታሪክ ነው።
ትጉህ እና ድንቅ አትዮጵያዊው ልጅ የወንድወሰን መንገሻ በባልደረቦቻቸው እና በመንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ዘንድ ሰፊ ክብር ያሰጡዋቸው አዕምሯዊ ችሎታቸው፣ የሀገራቸውን እድገት ለማፋጠን ያሳዩት ቁርጠኝነት እና ከሌሎች ጋር ተስማምቶ የመሥራት ችሎታቸው። ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት የልጅ የወንድወሰን መንገሻን የአመራር ችሎታቸውን እና ለፍትሃዊነት ያላቸውን ጥልቀት በመመዘን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የሽልማት ድርጅት አምስት ባለአደራዎች ውስጥ አንዱ አድርገው ሾመዋቸዋል። በዚህም ኃላፊነት ከ10 ዓመታት በላይ አገልግለዋል።
ልጅ የወንድወሰን መንገሻ እ ኤ አ 1974 ዓም በሚያዝያ ወር ዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የአይ ኤም ኤፍ (IMF) ስብሰባ በመሳተፍ ላይ እንዳሉ በኢትዮጵያ የነበረው ሁኔታ አደገኛ እየሆነ መጣ። ሁኔታው እርሳቸውንና ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ከሚወዷት ሀገራቸው የለያቸው እና ማለቂያ የሌለው የመሰለው አሳዛኝ የግዳጅ ግዞት ዘመን መጀመሪያ ነበር። ባለቤታቸው እና ሦስቱም ልጆቻቸው ከእርሳቸው ጋር ለመሆን ወደ አሜሪካ መጓዝ ቻሉ። ልጅ የወንድወሰን ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ጥሩ አማራጭ እንዳልሆነ ከተረዱ በኋላ ቅድሚያ የሰጡት ቤተሰቡን የሚያስተዳድሩበት በተለይም ልጆቻቸውን ለማስተማር የሚያስችል ሥራ መፈለጉን ነበር።
በዓለም አቀፍ ፋይናንስ መስክ በነበራቸው ሰፊ ዕውቀት እና ችሎታ ለንደን በሚገኘው First Boston Corporation (ፈርስት ቦስተን ኮርፖሬሽን) ሥራ ለማግኘት በቁ። ቀጥሎም በታማኝነታቸው እና በልዩ ችሎታቸው ወደ ማኔጂንግ ዳይሬክተርነት (Managing Director)
ደረጃ ዕድገት አገኙ። በኩባንያው ውስጥ ለብዙ ዓመታት በጥሩ መሪነት ከአገለገሉ በኃላ Associated African Financial Services (አሶሽየትድ አፍሪካን ፋይናንሽያል ሰርቪስስ) የሚባል የአማካሪ ድርጅት አቌቁመው በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጉልህ በሆኑ ፕሮጀክቶች ላይ ከአሥር አመታት በላይ ሠርተዋል።
ልጅ የወንድወሰን መንገሻ በቀሪው ሕይወታቸውም እንደሁልጊዜው ሌሎችን ለመርዳት፣ ሀገራቸው እና ሕዝቡ ላደረገላቸው ውለታ ለመመለስ ትኩረት በማድረጋቸው ብዙ የበጎ አድራጎት ቡድኖችን፣ ቤተክርስቲያናትን እና ግለ ሰቦችን ከመርዳት ተቆጥበው አያውቁም። ቤቱ ይቁጠረው እንደሚባለው ሰው የማያውቀው አምላክ ግን የሚያየው ብዙ ችግረኛችን ደግፈዋል። በተለይ ኅብረተሰቡን ለመርዳት ካቋቋሙዎቸው ቅርሶች አንዱ ለውድ አባታቸው መታሰቢያ እንዲሆን ባሕር ዳር ውስጥ የከፈቱት “አባ መንገሻ ገነሜ የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት እና የመረጃ ማዕከል” ነው።
ወጣቶች ትምህርታቸውን በትጋት እንዲቀጥሉ እና በሙሉ አቅማቸው ዓላማቸውን ለማሳካት እንዲጥሩ ለማበረታታት እና ለመደገፍ በምንም ዓይነት ወደኃላ አዩሉም ነበር። በተለይም ለከፍተኛ ትምህርት እድሎችን ለማስፋት ከነበራቸው ጽኑ ፍላጎት በራሳቸው እና በባለቤታቸው ወይዘሮ ሕይወት ስም በሃርቫርድ ቢዝነስ ትምህርት ቤት የትምህርት ብቃት ላላቸው የአፍሪቃውያን ተማሪዎች ስኮላርሺፕ አቋቀቁመው ብዙ ተማሪዋች ሊጠቅሙ ችለዎል።
በፍቅር ወንድዬ ተብለው የሚጠሩትን ልጅ የወንድወሰን መንገሻን የማወቅ ዕድል ያገኙ ሁሉ ተንከባካቢነታቸውን፣ ትሁትነታቸውን እና ለጋሥነታቸውን ይመሰክራሉ። ዘመዶችን፣ ጓደኞችን እንዲሁም ሌሎች ሰዎች መርዳት እና ምክር በመለገስ ረገድ የተቻላቸውን ሁሉ አድርገዋል። እንዲሁም ታዳጊ እና ወጣት የሆኑት ዘመዶቻቸው እንደአባት እና አማካሪ ያዩዋቸው ነበር። የቤተሰብ አባላት ታማኝነታቸውን እና ጥበባዊ ምክራቸውን ከፍ አድርገው ይመለከቷቸው ነበር። በተለይም የቅርብ ዘመዶቻቸው ከሆኑት ከራሥ አንዳርጋቸው መሳይ እና ከልዕልት ተናኘወርቅ ኃይለ ሥላሴ ፍቅር እና አክብሮት ምንግዜም አልተላያቸውም።
ልጅ የወንድወሰን እ ኤ አ ጥቅምት 12 ቀን 2025 በለንደን በሚገኘው ቤታቸው በቤተሰብ ተከበው በሰላም በማረፍ ከዚህ አለም ተለይተዋል።
በነሐሴ 23 ቀን 1UG4 ዓም እኤአ በትዳር ካገቡዋቸው ከውድ ባለቤታቸው ከወ/ሮ ሕይወት ጋር በፍቅር፣ በመከባበር እና በተድላ የዕድሜ ባለፀጋ ሆነው ያሬድ፣ ያድዋ እና የአደይን አፍርተዋል። የሰባት የልጅ ልጆች አያት ለመሆን በቅተዋል – ካሌብ፣ ሶፊያ፣ ሉላዴይ (ሊሊ)፣ ጌሊላ፣ አሸር፣ ፀጋ እና ኢያሱ ። ቤተሰቡ መሪ አባት የነበሩትን በሞት በማጣታቸው በታላቅ ሀዘን ላይ ቢወድቁም አምላክ ረጅም ዕድሜ ስለሰጣቸው እና ቤተሰቡን ፍቅር በተሞላበት አርአያነት በመምራታቸው በምስጋና ተሞልተዋል።
እኚህ ትሁት የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ፣ ቅዱስ ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 13 ላይ እንዳስተማረው የፍቅር ምሳሌ ሆነው ኖረዋል።
“ፍቅር ታጋሽ ነው፣ ፍቅር ደግ ነው፣ ፍቅር አይመቀኝም፣ ፍቅር አይታበይም፣ ፍቅር አይኰራም፣ ፍቅር ስነስርዓተቢስ አይደለም፣ ፍቅር የራሱን ጥቅም ብቻ ፈላጊ አይደለም፣ ፍቅር አይበሳጭም፣ ፍቅር ቢበደልም እንኳ በደልን እንደበደል አይቆጥርም፣ ፍቅር እውነት በሆነ ነገር ይደሰታል እንጂ ክፋት በሆነ ነገር አይደሰትም፣ ፍቅር ሁሉን ችሎ ይታገሳል፣ ፍቅር በሁሉም ላይ ተስፋ የደርጋል፣ ፍቅር በሁሉም ነገር ይጸናል”
ቸሩ አምላክ ነፍሳቸውን የዘላለም እረፍት ይስጥልን።
ቤተሰቡ ጓደኞቻቸው እና ዘመዶቻቸው ለላኩት አጽናኝ መልእክቶች እና የሀዘን መግለጫዎች ሁሉ ልባዊ ምስጋናቸውን ያቀርባሉ።ልጅ የወንድወሰን መንገሻ
ታሕሣስ 24 ቀን 1U20 ዓም – ጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓም
የሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የግራጅዌት ቢዝነስ ትምህርት ቤት የታላቅ አገልግሎት እና ለቀድሞ ተማሪዎች የሥራ ስኬት ተብሎ የተሰየመውን ሽልማት ለልጅ የወንድወሰን መንገሻ እ ኤ አ በ1UUG ዓም ሲሰጣቸው በመጀመሪያ የሳቸውን ማንነት መገለጫ ያደረገው “ሰብዓዊነትን የረዱ” በማለት እና በምስጋናው መዝጊያ ላይ ደግሞ “ለዓለም ደህንነት የታቻላቸውን አስተዋጽኦ ያበረከቱ” ሲል ዩኒቨርስቲው አድናቆቱን በሚገባ ገልጿል።
የተከበሩ አባታቸው አባ መንገሻ ገነሜ (ቀደም ሲል ፊታውራሪ) የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመድ ነበሩ። እናታቸው ወይዘሮ ተዋበች ዛማኑኤል በወራሪው ፋሽስት በግፍ ታሥረው በተወሰዱበት ኢጣልያ አገር ውስጥ ሕይወታቸው አለፏል። አክስታቸው ወ/ሮ ሉልአደይ ዛማኑኤል ልጅ የወንደሰንን እና ታናሽ እህቶቻቸውን ወ/ሪት ኮከቤ መንገሻን እና ወ/ሮ እግዚሐርያ መንገሻን እንደ ልጆቻቸው በፍቅር አሳድገዋቸዋል። ልጅ ከበደ ኃይሌ ታላቅ ወንድማቸው ነበሩ።
ልጅ የወንድወሰን የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በተፈሪ መኮንን እና በፕሪንቺፔ ዲ ፒያሞንቴ ትምህርት ቤቶች ከተማሩ በኋላ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አቃቂ በሚገኘው የአድቬንቲስት ሚሲዮን እና አዲስ አበባ በሚገኘው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተምረው አጠናቅቀዋል። ቀጥሎም፣ በጊዜው የላንደን ዩኒቨርሲቲ አካል የነበረው ሳውዝሃምፕተን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተቀብሏቸው በኢትዮጵያ መንግሥት የነፃ ትምህርት ዕድል ድጋፍ ተምረው እ ኤ አ በ 1U54 ዓም በኢኮኖሚክስ እና አካውንቲንግ በከፍተኛ ማዕርግ ተመረቁ። ኮሌጅ የተማረ የመጀመሪያው የቤተሰቡ አባል እንደመሆናቸው መጠን ወደ እናት አገራቸው ሲመለሱ ሌሎችን ለመርዳት ይጓጉ ነበር። እውቀታቸውን እና ተሞክሯቸውን ለማስፋት ወደ አሜሪካ ሲጓዙ አስፈላጊው ገንዘብ ስላልነበራቸው ቦስተን ለመድረስ ወደካናዳ በሚጓዝ አንስተኛ የውቅያኖስ መስመር ላይ በአስተናጋጅነት በመሥራት ሃሳባቸውን አሳክተዋል። ከእዚያም እ ኤ አ በ1U5G ዓም ከሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በኤም ቢ ኤ (MBA) ዲግሪ ተመረቁ።
ልጅ የወንድወሰን መንገሻ ወደ ኢትዮጵያ ከመመለሳቸው በፊት ዶክተር አልበርት ሸቫይጸርን ለማግኘት ምዕራብ መካከለኛው አፍሪቃ ውስጥ ሩቅ ሥፍራ ወደሚገኝ ሆስፒታል ተጓዙ። ሆስፒታሉ ውስጥ ሁለት ሳምንታት ከቆዩ በኋላ ዶክተር ሸቫይጸርን የመሰለ ሌሎችን ለመርዳት የወሰኑ ሰውን መተዋወቅ ለወጣቱ ምሩቅ ታላቅ ክብር ነበር። በሆስፒታሉ ያጋጠማቸው ተሞክሮ በአገራቸው ሕዝብ ሕይወት ላይ ለውጥ ለማምጣት እራሳቸውም በቁርጠኝነት እንዲሰለፉ አድርጓቸዋል።
ወደ የሚወዷት አገራቸው ከተመለሱ በኋላ የመጀመሪያ ሥራ ምድባቸው በኢትዮጵያ አየር
መንገድ የከፍተኛ ማኔጅመንት ኃላፊነት ነበር። ቀጥሎም በገንዘብ ሚንስቴር የዳይሬክተርነት ሹመት አገኙ። በዚሁ ሥራቸው ላይ እንዳሉም በወቅቱ በልዑል ራሥ መንገሻ ሥዩም በሚመራው የኢትዮዽያ የአየር መንገድ ቦርድ አባል በመሆን አየር መንገዱ በተለይ አፍሪቃ ውስጥ በተሳካ ሁኔታ የተለያዩ የብሪያ መስመሮችን እንዲዘረጋ የአባልነታቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዎል። የመጀመሪያዎቹን ቦይንግ ጄት አኤሮፕላኖች ለመግዛት በተደረገው ወሳኝ ድርድር ውስጥ ቁልፍ ሚና ነበራቸው።
በ1UG0 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ሆነው ተሾሙ። ይህንን የተከበረ ቦታ ለመያዝ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ነበሩ። የባንኩን ተቋም ለማዘመን ጠቃሚ ተነሳሽነቶችን በመምራት እና በማስተባበር ለአሥራ አራት ዓመታት በዚያ ሥራ ላይ ቆይተዋል። ከብዙ ትሩፋቶቻቸው አንዱ የብሔራዊ ባንክ ሠራተኞችን ለተጨማሪ ሥልጠና ወደ ውጭ አገር ለመላክ ያደረጉት ብርቱ ጥረት እና ስኬታማ ተነሳሽነት ነበር። ይህ በአርቆ አሳቢነት ላይ የተመሠረተ ጥረት ቁጥራቸው እየጨመረ ለመጣው ልዩ የባንክ ሥራ መደቦች በሙያው የሠለጠኑ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያትን መመደብ አስችሏል።
ልጅ የወንድወሰን መንገሻ የኢትዮጵያ መንግሥትን ወክለው ከሌሎች ሀገሮች የገንዘብ ሚኒስትሮች ጋር በመተባበር በዓለም አቀፍ የባንክ ማኅበረሰብ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ አድርገዋል። በተለይም ልጅ የወንድወሰን መንገሻ የአፍሪቃን ኤኮኖሚ ለማሳደግ እና ድህነትን ለመቀነስ የታለመውን የአፍሪቃ ልማት ባንክን (AfDB) በሚመሠረትበት ጊዜ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል። ኢትዮጵያ መሥራች ባለአክሲዮን እንደመሆኗ መጠን ባንኩን በማቋቋም ረገድ ግንባር ቀደም እና ስኬታማ መሪነት አሳይታለች። ብዙዎች ይህንን ስኬት የብሔራዊ ባንክ ገዥ የአቶ ምናሴ ለማ እና ምክትል ገዥ የልጅ የወንድወሰን መንገሻ አርቆ አስተዋይነት እና አመራር ውጤት ነው ብለው ይመለከቱታል። በዓለም አቀፍ ፋይናንስ ላይ በነበራቸው ዕውቀት እና ባለራዕይ አመራር በ1U80ዎቹ ዓመታት አፍሪቃ ልማት ባንክ ካፒታሉን ለማሳደግ ክልላዊ ያልሆኑ ሀገራትም
(non-regional countries) እንዲሳተፉ መንገድ ከፍተዋል። ይህም ዛሬ የባንኩ የስኬት ታሪክ ነው።
ትጉህ እና ድንቅ አትዮጵያዊው ልጅ የወንድወሰን መንገሻ በባልደረቦቻቸው እና በመንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ዘንድ ሰፊ ክብር ያሰጡዋቸው አዕምሯዊ ችሎታቸው፣ የሀገራቸውን እድገት ለማፋጠን ያሳዩት ቁርጠኝነት እና ከሌሎች ጋር ተስማምቶ የመሥራት ችሎታቸው። ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት የልጅ የወንድወሰን መንገሻን የአመራር ችሎታቸውን እና ለፍትሃዊነት ያላቸውን ጥልቀት በመመዘን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የሽልማት ድርጅት አምስት ባለአደራዎች ውስጥ አንዱ አድርገው ሾመዋቸዋል። በዚህም ኃላፊነት ከአስር ዓመታት በላይ አገልግለዋል።
ልጅ የወንድወሰን መንገሻ እ ኤ አ 1U74 ዓም በሚያዝያ ወር ዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የአይ ኤም ኤፍ (IMF) ስብሰባ በመሳተፍ ላይ እንዳሉ በኢትዮጵያ የነበረው ሁኔታ አደገኛ እየሆነ መጣ። ሁኔታው እርሳቸውንና ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ከሚወዷት ሀገራቸው የለያቸው እና ማለቂያ የሌለው የመሰለው አሳዛኝ የግዳጅ ግዞት ዘመን መጀመሪያ ነበር። ባለቤታቸው እና ሦስቱም ልጆቻቸው ከእርሳቸው ጋር ለመሆን ወደ አሜሪካ መጓዝ ቻሉ። ልጅ የወንድወሰን ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ጥሩ አማራጭ እንዳልሆነ ከተረዱ በኋላ ቅድሚያ የሰጡት ቤተሰቡን የሚያስተዳድሩበት በተለይም ልጆቻቸውን ለማስተማር የሚያስችል ሥራ መፈለጉን ነበር።
በዓለም አቀፍ ፋይናንስ መስክ በነበራቸው ሰፊ ዕውቀት እና ችሎታ ለንደን በሚገኘው First Boston Corporation (ፈርስት ቦስተን ኮርፖሬሽን) ሥራ ለማግኘት በቁ። ቀጥሎም በታማኝነታቸው እና በልዩ ችሎታቸው ወደ ማኔጂንግ ዳይሬክተርነት (Managing Director) ደረጃ ዕድገት አገኙ። በኩባንያው ውስጥ ለብዙ ዓመታት በጥሩ መሪነት ከአገለገሉ በኃላ Associated African Financial Services (አሶሽየትድ አፍሪካን ፋይናንሽያል ሰርቪስስ) የሚባል የአማካሪ ድርጅት አቌቁመው በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጉልህ በሆኑ ፕሮጀክቶች ላይ ከአሥር አመታት በላይ ሠርተዋል።
ልጅ የወንድወሰን መንገሻ በቀሪው ሕይወታቸውም እንደሁልጊዜው ሌሎችን ለመርዳት፣ ሀገራቸው እና ሕዝቡ ላደረገላቸው ውለታ ለመመለስ ትኩረት በማድረጋቸው ብዙ የበጎ አድራጎት ቡድኖችን፣ ቤተክርስቲያናትን እና ግለ ሰቦችን ከመርዳት ተቆጥበው አያውቁም። ቤቱ ይቁጠረው እንደሚባለው ሰው የማያውቀው አምላክ ግን የሚያየው ብዙ ችግረኛችን ደግፈዋል። በተለይ ኅብረተሰቡን ለመርዳት ካቋቋሙዎቸው ቅርሶች አንዱ ለውድ አባታቸው መታሰቢያ እንዲሆን ባሕር ዳር ውስጥ የከፈቱት “አባ መንገሻ ገነሜ የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት እና የመረጃ ማዕከል” ነው።
ወጣቶች ትምህርታቸውን በትጋት እንዲቀጥሉ እና በሙሉ አቅማቸው ዓላማቸውን ለማሳካት እንዲጥሩ ለማበረታታት እና ለመደገፍ በምንም ዓይነት ወደኃላ አዩሉም ነበር። በተለይም ለከፍተኛ ትምህርት እድሎችን ለማስፋት ከነበራቸው ጽኑ ፍላጎት በራሳቸው እና በባለቤታቸው ወይዘሮ ሕይወት ስም በሃርቫርድ ቢዝነስ ትምህርት ቤት የትምህርት ብቃት ላላቸው የአፍሪቃውያን ተማሪዎች ስኮላርሺፕ አቋቀቁመው ብዙ ተማሪዋች ሊጠቅሙ ችለዎል።
በፍቅር ወንድዬ ተብለው የሚጠሩትን ልጅ የወንድወሰን መንገሻን የማወቅ ዕድል ያገኙ ሁሉ ተንከባካቢነታቸውን፣ ትሁትነታቸውን እና ለጋሥነታቸውን ይመሰክራሉ። ዘመዶችን፣ ጓደኞችን እንዲሁም ሌሎች ሰዎች መርዳት እና ምክር በመለገስ ረገድ የተቻላቸውን ሁሉ አድርገዋል። እንዲሁም ታዳጊ እና ወጣት የሆኑት ዘመዶቻቸው እንደአባት እና አማካሪ ያዩዋቸው ነበር። የቤተሰብ አባላት ታማኝነታቸውን እና ጥበባዊ ምክራቸውን ከፍ አድርገው ይመለከቷቸው ነበር። በተለይም የቅርብ ዘመዶቻቸው ከሆኑት ከራሥ አንዳርጋቸው መሳይ እና ከልዕልት ተናኘወርቅ ኃይለ ሥላሴ ፍቅር እና አክብሮት ምንግዜም አልተላያቸውም።
ልጅ የወንድወሰን እ ኤ አ ጥቅምት 12 ቀን 2025 በሎንዶን በሚገኘው ቤታቸው በቤተሰብ ተከበው በሰላም በማረፍ ከዚህ ዓለም ተለይተዋል።
በነሐሴ 23 ቀን 1964 ዓም እኤአ በትዳር ካገቧቸው ከውድ ባለቤታቸው ከወ/ሮ ሕይወት ግሬታ መንገሻ ጋር በፍቅር፣ በመከባበር እና በተድላ የዕድሜ ባለፀጋ ሆነው ያሬድ፣ ያድዋ እና የአደይን አፍርተዋል። የሰባት የልጅ ልጆች አያት ለመሆን በቅተዋል – ካሌብ፣ ሶፊያ፣ ሉላዴይ (ሊሊ)፣ ጌሊላ፣ አሸር፣ ፀጋ እና ኢያሱ ። ቤተሰቡ መሪ አባት የነበሩትን በሞት በማጣታቸው በታላቅ ሀዘን ላይ ቢወድቁም አምላክ ረጅም ዕድሜ ስለሰጣቸው እና ቤተሰቡን ፍቅር በተሞላበት አርአያነት በመምራታቸው በምስጋና ተሞልተዋል።
እኚህ ትሁት የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ፣ ቅዱስ ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 13 ላይ እንዳስተማረው የፍቅር ምሳሌ ሆነው ኖረዋል።
“ፍቅር ታጋሽ ነው፣ ፍቅር ደግ ነው፣ ፍቅር አይመቀኝም፣ ፍቅር አይታበይም፣ ፍቅር አይኰራም፣
ፍቅር ስነስርዓተቢስ አይደለም፣ ፍቅር የራሱን ጥቅም ብቻ ፈላጊ አይደለም፣ ፍቅር አይበሳጭም፣ ፍቅር ቢበደልም እንኳ በደልን እንደበደል አይቆጥርም፣ ፍቅር እውነት በሆነ ነገር ይደሰታል እንጂ ክፋት በሆነ ነገር አይደሰትም፣ ፍቅር ሁሉን ችሎ ይታገሳል፣ ፍቅር በሁሉም ላይ ተስፋ የደርጋል፣ ፍቅር በሁሉም ነገር ይጸናል”
ቸሩ አምላክ ነፍሳቸውን የዘላለም እረፍት ይስጥልን።