መጽሀፎች ታትመው ሳይወጡ በፊት ደራሲው አእምሮ ውስጥ ነበሩ፡፡ ከዚያ ወረቀት ላይ ሰፍረው ተተይበው በቂ አርትኦት ተሰርቶላቸው ወይም ተሰርቶባቸው ወደ ማተሚያ ቤት ይላካሉ፡፡ የበአሉ ግርማ ሀዲስ የተሰኘው ልቦለድ ድርሰቱ ጥር 24 1974 ነበር እንዲታተም ፈቃድ የተጠየቀለት፡፡
በጊዜው የኢትዮጵያ መጽሀፍት ድርጅት የአሳታሚው ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ አማረ ማሞ ለ ማስታወቂያ እና መርሀ-ብሄር ሚኒስቴር የስነ-ጽሁፍ ምርመራ ክፍል ብለው መጽሀፉ ተመርምሮ እንዲፈቀድ እናሳስባለን ሲሉ ደብዳቤ ጽፈው ነበር፡፡
ከታች ያለውን ምስል ይመለከቷል፡፡ መጽሀፉ በታይፕ የተተየበው 398 ገጾች ሲኖሩት የተተየበው ረቂቅ ምን መልክ እንደነበረው ሊመለከቱ ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ሀሳቦት የራይት ምልክት የተደረገባቸው ሳንሱር ያለፉ ሲሆኑ በብእር የተነካኩት ደግሞ የሚሻሻሉ ሀሳቦች ናቸው፡፡ ሀዲስን ያነበባችሁ ይህን ረቂቅ በጨረፍታ እዩትና ለበአሉ ያላችሁን አክብሮት ግለጹ ፡፡