ቶፕ 3 በዩቲዩብ ተመልካች ያገኙ የፋና ተወዳጅ መሰናዶዎች

በፋና ቲቪ ላይ በርካታ መሰናዶዎች ይቀርባሉ ብዙዎቹ እውነት ለመናገር ተመራጭና ተወዳጅ ናቸው፡፡ እነዚህ መሰናዶዎች ደግሞ በዩቲዩብ ላይ ተጭነው ተደራሽነታቸው ከፍ እንዲል ይደረጋል፡፡ እነዚህንም የተጫኑ ቪድዮዎች ማንም ሰው የፈለገበት ሀገር ሁኖ ይመለከታል፡፡

የጎግል አንድ አካል የሆነው ዩቲዩብም በርካታ ተመልካች ፤ ላይክና አስተያየት ያላቸውን ቪድዮዎች ያሳውቃል፡፡ እንደሚታወቀው ዩቲዩብ ክፍያ የሚከፍለው በተመልካች ብዛት ሲሆን ስንት ሰው ላይክ ብሎታል የሚለውም ግምት ውስጥ ይገባል፡፡ በዚህ መሰረት እኔ ባደረግኩት ምጥን ዳሰሳ በዚህ 3 ወር ውስጥ 3 ጋዜጠኞች የሰሩት ስራ በርካታ ተመልካች አግኝቶአል፡፡

ይህን ዳሰሳ በግሌ የሰራሁት መሆኑ ይታወቅልኝ፡፡ ስለሆነም በደረጃ ማስቀመጥ አስፈላጊ ስለሆነ በጸጋዬ ንጉስ የተሰራው ‹‹አሻራ አምጡ የተባሉት የዱባይ ተጓዦች እና የፖሊስ ውዝግብ›› የተሰኘው ዜና Feb 22, 2018 ፖስት የተደረገ ሲሆን አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 92‚426 ተመልካች በማግኘት አንደኛ ሲሆን 446 ላይክም አለው ፡፡ 387 ሰዎችም በዜናው ላይ ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡

ሁለተኛ በመሆን ደግሞ ‹‹የኢትዮጵያን ስም በዓለም አቀፍ ደረጃ ያስጠሩ›› የሚለው መሰናዶ ሲሆን Feb 20, 2018 ፖስት የተደረገ ነበር፡፡ ይህ መሰናዶ 90‚162 ተመልካች ያገኘ ሲሆን 1023 ላይክና 129 ኮሜንት ያገኘ ነው፡፡ አዘጋጅዋ ደግሞ ለምለም ዮሀንስ ናት፡፡ ይህ ቪድዮ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው እንዲህ አይነት ሰፊ ተቀባይነት ያገኘው፡፡

በ3ኛነት ደግሞ ያለው ‹‹ብዙዎችን ያስገረመው የኢትዮጵያውያኑ ህፃናት ምጡቅነት›› የሚለው መሰናዶ ሲሆን 73‚779 ሰዎች የተመለከቱት ሲሆን 1434 ላይክም አግኝቶአል፡፡ እንዲሁም 344 ኮሜንት አለው፡፡ የዚህ መሰናዶ አዘጋጅ ደግሞ ብስራት መንግስቱ ነው፡፡
ይህን ጥናት የሰራው ተወዳጅ ሚድያ ለጋዜጠኞቹ ከሚያሳትመው ሲዲ አንዱን በስጦታ ያበረክታል፡፡ በ0911416678 ይደወል፡፡


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *