ባምላክ ፀጋዬ- ተስፋ የሚጣልበት ወጣት የቲቪ ዳይሬክተር

      ከዕዝራ እጅጉ-(ተወዳጅ ሚድያ)

ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን እየሠሩ ያሉ በዕድሜ እስከ 26 ዓመት የሞላቸው በልዩ ልዩ ሙያ ላይ ያሉ ወጣቶችን ያበረታታል ። የሠሩት ሥራ ላይ ምርምር ያደርጋል። ተስፋ የተጣለባቸው እና ነገ ለኢትዮጵያ የሚጠቅም ነገር የመሥራት ዕድል ያላቸውን ዛሬ ከህዝብ ጋር እንዲተዋወቁ እናደርጋለን። ነገ ትልቅ ሥራ ሲሠሩ ደግሞ ቀትልቅ መዝገብ ላይ ስማቸውን ያሰፍራል። በዚህ መሠረት በማህበራዊ ድረ ገፆች ላይ አጭር ታሪካቸውን፣ምስላቸውን፣ ስለ እነርሱ የተሰጡ ምስክርነቶችን እና የሥራዎቻቸውን ሊንኮች እናወጣለን። የዛሬ ተስፈኛ የነገ መድረሻው ትልቅ እንደሆነ የፀና ዕምነት አለን።

ይህን ስናደርግ ወጣት ባለሙያዎቹ ከሰው ጋር ለመተዋወቅ ዕድል ይፈጠርላቸዋል። ሌሎች ወጣቶችም እኛም ጠንክረን አቅማችንን ብናወጣ አበርክቷችን ይጻፋል በሚል ሞራል ተነሳስተው አንድ ቁምነገር ሊሠሩ ይችላሉ ብለንም እናምናለን።

በመሆኑም የሥራ ታሪካቸው ሌሎችን ያበረታታል ብለን ዕምነት ከጣልንባቸው ፣ተስፋ አላቸው ብለን ካመንባቸው መካከል ባምላክ ፀጋዬ አንዱ ነው። ባምላክ የ 26 ዓመት ወጣት ሲሆን በፋና ሚድያ ኮርፖሬሽን በቲቪ ዳይሬክተርነት እያገለገለ ይገኛል። እርሱ ዳይሬክት ያደረጋቸው ቅንብሮች በባለሙያዎች ዘንድም በጥራታቸው እና ፈጣራዊነት የታከለባቸው በመሆናቸው ይደነቃሉ። በመሆኑም የባምላክን ማንነት በአጭሩ እናቀርባለን። ዕዝራ እጅጉ ታሪኩን እንደሚከተለው አጠናክሮታል ።

#

የቴሌቪዥን ፕሮዳክሽን ዳይሬክተር ባምላክ ፀጋዬ በ1991 ዓ.ም በወሊሶ ከተማ ነው ትውልዱ። የቋንቋ አስተማሪ በሆነው ወላጅ አባቱ የሥራ ዝውውር ምክንያት ዕድገቱና አብዛኛው የትምህርት ህይወቱ በወልቂጤ ከተማ ላይ ነበር።

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ሮሆቦት አካዳሚ 92 በመቶ ከ8ወደ ዘጠኝ ማለፊያ ነጥብ አምጥቷል።
ሁለተኛ ደረጃ አበሩስ ደግሞ ወልቂጤ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ 4ነጥብ የ10ክፍል ውጤት አመጣ።
12ኛ ክፍል አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ደራርቱ ቱሉ ትምህርት ቤት ተማረ።
በቴአትር ጥበባት ከወልቂጤ ዩኒቨርሰቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ሲይዝ 3.88 ጂፒኤ ነበር ያመጣው።
በአማተር ክበባት እንቅስቃሴ ወልቂጤ ከተማ ውስጥ ጆካ አበሩስ የኪነ ጥበብ ቡድን ጋር በስነ ፅሁፍ ፣ድርሰትና፣ አዘጋጅነት፣በሥነፅሁፍ ምሽቶች ላይ የኪነ ጥበብ አቅምና ክህሎቱን ያሳየ ነው።
12ኛ ክፍል ሳለ አዲስ አበባ የትምህርት ቤቶች የኪነ ጥበብ ውድድር ላይ በግጥምና ስዕል ተሸላሚ ነበር።

በዩኒቨርሲቲ ቆይታውም ውጤታማ 4 አመታትን አሳልፏል።

በዝግጅት ውድነህ ክፍሌ ባቢሎን በሳሎን፣ በ ስፔናውያን ደራሲዎች Serafin and Joaquin Alvarez Quintero የተፃፈውን Sunny morning ቴአትርን በ መልቲ ሚዲያ የዝግጅት ቅርፅ ፣አኒብ ቱፊታዊ ቴአትር፣እንዳለጌታ ከበደ የካሳ ፈረሶች ቴአትር፣የመልካሙ ዘሪሁን ህንደኬ በመምህራን ታዳሚዎች የተወደዱና በከፍተኛ ነጥብ ኮርሱን የሚያልፉ ቴአትሮችን በአዘጋጅነት ከዩኒቨርስቲው ጎን ለጎን በጉራጌ ዞን ባህል ቡድን ለተለያዩ ክልል አቀፍና ሀገር አቀፍ ሁነቶች ቱፊታዊ ድራማዎች በድርሰት ፅሁፍ በዝግጅትና ትወና save the children በሚያዘጋጀው ሀገርኛ
የህፃናት የተረት መፅሀፍት ላይ በ ኢሉስትሬተር ( የመፅሀፍት ዲዛይንና ስዕል) አቅሙን አሳይቷል።

ባምላክ በዳይሬክቲንግ፣ስዕል፣ፕሮዳክሽን ዲዛይኒንግ ችሎታ አለው።ከተመረቀም በኃላ በተቋም ደረጃ በኤን ቢሲ ኢትዮጵያ ጋዜጠኝነት በዜና አንባቢነት ለአንድ ዓመት አገልግሎት ሰጥቷል።

በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በፕሮዳክሽን ዳይሬክተርነት ላለፉት 2 ዓመታት የሠራ ሲሆን የፋና ላምሮት 5ኛውን የአሸናፊዎች አሸናፊ ሙሉ የ 3 ወር ውድድር(12 ሳምንት) እስከ ፍፃሜው በዳይሬክቲንግ ሠርቷል።

በፋና ቴሌቪዥን፣ የአዕላፋት ዝማሬ ዳይሬክቲንግ ፣የቀጥታ ስርጭቶች የበዓላት እና ሁነቶች የጣቢያ የፕሮግራምና የድርጅት ማስታወቂያዎችን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለዕይታ አቅርቧል።

ባምላክ፣ የቤተሰቡ የመጨረሻ ልጅ ሲሆን አባቱ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህር እና የሥነ ፅሁፍ ችሎታና ዝንባሌ ያላቸው ኪነጥበብ የሚወዱ ባምላክን በትምህርቱና በፍላጎቱ የሚያበረታቱ ናቸው። እናቱ የቤት እመቤት እና በጎ ፍቃደኛ የኪነ ጥበብ ወዳጅ፣ በስራውም በትምህርቱም ደጋፊው ናቸው። 3 እህቶች 1 ወንድም አለው።
“…በቤተሰብ ውስጥ ከፍተኛ የኪነጥበብ ፍቅር አለ። እናትና አባቴም እህቶቼም የአማተር ኪነጥበብ ቡድን ውስጥ ይሠሩ የነበሩ መተወን የሚወዱ ነበር።” በማለት ባምላክ አጫውቶናል።

  ተጨማሪ፦

SOAS university of London አሠርቶ በብሔራዊ ከቴአትር በቀረበው ቴራኒያ ኮኮይሳኒ መልቲ ሚዲያ ቴአትር በአርት ዳይሬክተርነት፣
በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤርሙዳ ቴአትር የበኩር ፍርድ ተከታታይ ድራማ ፣ቶኔቶር ተከታታይ ድራማ፣ያለ ነብስ( የጉማ አዋርድ እጩ የነበረ)፣ልባም ደሀ፣ጀምበር ፊልሞች ላይ ገፅ- ቅብ ሜክ አፕ ዲዛይን ሠርቷል።

ባምላክ የሚሠራው የቴሌቪዥን ፕሮዳክሽን ዳይሬክተር ማለት
የመነሻ ሀሳብ በመውሰድ ወይም ሊሠራ የታሰበን ፕሮግራም ፎርማት ይዘቱን በመመልከት ሀሳቡን በመረዳት ወደ ምስል መቀየር ነው። በዚህም ሂደት ለይዘቱ የሚስማማ አቅራቢ(ተዋናይ) የቀረፃ ቦታ፣የካሜራ አጠቃቀም፣ የብርሀን፣ ድምፅና የምስል ቅንብርን ጨምሮ በአጠቃላይ በስክሪኑ የሚታየውን ምስል ከሀሳብ እስከ ስርጭት የሚሰራ ባለሙያ ነው። የቴሌቪዥን ዳይሬክተሮች ከሌላው የተንቀሳቃሽ ምስል ዳይሬክተሮች የሚለዩት ያለ ምንም ኤዲቲንግ በቀጥታ ለሚሠሩ ስርጭቶች ችሎታ የሚያስፈልጋቸው መሆኑ ነው። ይህም ሲባል አስቀድመው ዝግጅት በማድረግ በርከት ያሉ (ብዙ ጊዜ ከ አስር በላይ) ካሜራዎችን ሌሎችንም የስርጭት መሳሪያና ባለሙያዎችን በመምራት የተፈለጉት ምስሎች በተገቢው ሁኔታ ለተመልካች እንዲደርሱ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ከታች የተቀመጡትን ሊንኮች የባምላክን ሥራዎችን የሚያሳዩ ናቸው።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ወርቁ ሙሉነህ ባምላክን ያስተማሩ ሲሆን ትልቅ አቅም ያለው፣ ከሁሉም ለመማር ራሱን ያዘጋጀ፣ የፈጠራ ክህሎትን የታደለ ሲሉ መስክረውለታል። የፋና ቲቪ ሰዎችንም አመራሮችንም አነጋግረን ሁሉም በአንድ ድምፅ ድንቅ አቅም ያለው ሲሉ ተናግረውለታል።

https://www.youtube.com/live/biJtCL3a770?feature=shared
https://youtu.be/ASze9wvWFds?feature=shared
https://www.facebook.com/share/v/17PjFv7kJc/
https://youtu.be/s9212079qOc?feature=shared
https://www.facebook.com/share/v/171jAj7LaG/
https://youtu.be/ia9nH75fc-c?feature=shared
https://youtu.be/C5Dut0HTId0?feature=shared
https://youtu.be/50So-arpFn8?feature=shared
https://youtu.be/ZjYpJUtZvQk?feature=shared
https://youtu.be/U-XoHK0zd4I?feature=shared

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *