በዓሉ ግርማ ለራሱ የቅጣት ደብዳቤ መጻፉ ን ያውቃሉ ?

ሰነዶች በወጉ ከታዩ ብዙ ይናገራሉ ። ጊዜው የካቲት 5 1968 ነበር ። በዓሉ ግርማ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት መምሪያ ሀላፊ ነበር ።

እንደ አቶ ግዮን ሀጎስ ያሉ ደግሞ የእንግሊዝኛ ዴስክ ሀላፊ በመሆን ያገለግሉ ነበር ። ታድያ በጊዜው ዜና ሲሰራ በተፈጠሩ 2 ስህተቶች በዓሉ ግርማን ጨምሮ 5 የኢዜአ ባልደረቦች ከ 15 ብር እስከ 30 ብር ተቀጥተው ነበር ።

ከታች የሰፈረው ደብዳቤ ዝርዝር ጉዳዮችን ይዟል ።የሚገርመው በዓሉ ግርማ በራሱ ፊርማ እና የማህተም ቲተር ወጣ ደብዳቤ ራሱን መቅጣቱ ነው። የዛሬ 47 ዓመት ከ 6 ወር ይህ ታሪክ ሲፈጸም የምታውቁ አንድ ነገር አካፍሉን ። እኛ ደብዳቤውን እጃችን ከገባው 7ገጾች ጋር አካፍለናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *