ኮስሞፖሊታን ሪል ስቴት ያስገነባቸውን የአፓርታማ ቤቶች አስመረቀ

ኮስሞፖሊታን ሪል ስቴት በቦሌ ጃፓን ኤምባሲ አቅራቢያ ሠርቶ ያጠናቀቀውን ጂ +11 የሆነ በ 700 ካሬሜትር ላይ ያረፈ ዘመናዊ ባለ ምቾት አፓርታማ ቤቶች በዛሬው እለት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት አስመርቋል ኮስሞፖሊታን ሪል ስቴት፣ በአሁኑ ሰዓት በአገራችን በቤቶች ግንባታ እና በሌሎች ዘርፎችም ላይ ተሠማርቶ የሚገኝ ድርጅት ሲሆን በዛሬው እለትም ቤቶቹን ለገዢዎች አስተላልፏል። ድርጅቱ፣ በይፋ ከተመሠረተ 5 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በእነዚህ ዓመታት ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠሩ ባሻገርም የመኖሪያ ቤት ችግርንም ለማቃለል የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል

ኮስሞፖሊታን የስሙ ትርጉም በአንድ ቦታ ተሰባስቦ የሚኖር የከተማ ማህበረሰብን የሚያመለክት ነው። ድርጅቱ እንደ ስሙ የከተማን ኑሮ ምቹ ለማድረግ ከመቼውም ጊዜ አስበልጦ እየሠራ እንደሚገኝ ተገልጿል ። በቦሌ ጃፓን ኤምባሲ አቅራቢያ ሠርቶ ያጠናቀቀው ጂ +11 የሆነ በ 700 ካሬሜትር ላይ ያረፈ ዘመናዊ ባለ ምቾት አፓርታማ የቤት ገዢዎችን ፍላጎት ያሟላ እንደሆነም የድርጅቱ የማርኬቲንግ እና ሽያጭ ሥራ መሪ ሜላት ጥላሁን ገልፃለች።
የስፖርት ማዘውተሪያ ጂም፣ሳዋናና ስቲም የተሟላላቸው የኮስሞፖሊታን መኖሪያ ቤቶች የ24 ሰዓት ኤሌክትሪክ የተመቻቸላቸው ናቸው ።

የኮስሞፖሊተን መኖሪያ ቤቶች በሙያው የላቀ ልምድ ባካበቱ የአገር ውስጥና የውጭ ባለሙያዎች የተገነቡ ሲሆን የቤቶቹ የአሠራር ጥራትም ደረጃውን የጠበቀ ነው። በዋጋም በተመጣጣኝ የቀረቡ እንደሆኑም ተገልጿል። ድርጅቱ፣ ይህን የግንባታ ስራ ሲያከናውን ለ250 ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል ። ኮስሞፖሊታን፣ በአሁኑ ሰዓት ኦሎምፒያ ጂ+17 ህንጻ እንዲሁም በፒያሳ ኤሊያና ሞል አካባቢ ለሱቅና ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የገበያ ማዕከል ግንባታ የሚጀምር ሲሆን ይህም ለበርካታ ኢትዮጵያዊያን የስራ ዕድል ይፈጥራል ። በአስመጪና ላኪነት ፣በቤት እና ቢሮ እቃዎች ፣በወረቀት ማምረት እንዲሁም በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የተሠማራው ኮስሞፖሊታን ለደንበኞቹ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት ቀዳሚ ግቡ መሆኑ ተነግሯል።
የመርሀ-ግብሩ አዘጋጅ እና የሚድያ ፣የህዝብ ግንኙነት ሥራውን ያከናወነው ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን ሲሆን በዕለቱም በተወዳጅ ሚድያ አማካኝነት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሠጥቷል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *